18ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን በዓል በፍትሕ ሚኒስቴር

The 18th National Flag Day celebration at the Ministry of Justice

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር “ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራት፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ሕዳሴ!” በሚል መሪ ቃል በዛሬዉ እለት በመላው አገሪቱ ተከብሮ የሚዉለዉን 18ኛዉን የሠንደቅ ዓላማ ቀን የተቋሙ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ብሎም ሰራተኞች በተገኙበት አክብሯል፡፡

የኢትዮጵያዊነት የማንነት ዓርማና መገለጫ የሆነዉ የብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን በሠንደቅ ዓላማ አዋጅ 863/2006 አንቀጽ 2 መሰረት በየዓመቱ ጥቅምት ወር በገባ በመጀመሪያዉ ሳምንት ሰኞ ዕለት እንደሚከበር የሚደነግግ ሲሆን ይህንኑ ተከትሎ በዛሬዉ እለት በዓሉ ተከብሮ ዉሏል፡፡

በዓሉ የሚከበርበት ዋና ዓላማም ለሠንደቅ ዓላማ የሚገባዉን ክብር በመስጠት ዜጎች የጋራ ዕሴቶቻቸዉን የሚያጠናክሩበትና በአገራዊ አንድነትና ኅብረ -ብሔራዊነት መግባባትን የሚፈጥሩበት አገራዊ በዓል መሆኑ ሲሆን ዘንድሮ ለ18ኛ ጊዜ በዓሉ ሲከበር የኢትየጵያዉያን ብሔራዊ ጥቅም ማሳያ የሆነዉ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ተመርቆ ስራ በጀመረበት ማግስት መሆኑ ለየት እንደሚያደርገዉም ተመላክቷል፡፡

በመጨረሻም የተቋሙ አመራርና ሰራተኞች በሠንደቅ ዓላማ ፊት ቆመዉ ቃለ መሀላ በመፈፀም ለአገራቸዉና ለሠንደቅ ዓላማቸዉ ያላቸዉን ክብርና ፍቅር ዳግም በመግለፅ የአገራቸዉን አንድነትና ሉአላዊነት ለማስጠበቅ ቃላቸዉን አድሰዋል፡፡

Tagged Under: 200 birr note 2006 agreement 2006 proclamation Access to Justice addis ababa justice bureau african charter on the rights and welfare of the child celebration Convention on the Rights of the Child convention on the rights of the child (crc) day ethiopian federal ministry of justice Ethiopian Ministry of Justice fdre ministry of justice federal ministry of justice Flag Justice Justice Ministry ministry ministry of justice (ethiopia) National national flag National Flag Day national justice plan national justice transformation national transitional justice policy ratio un convention on the rights of the child
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች

ተመሳሳይ ዜናዎች