በጠበቆች የግብር አከፋፈል ዙሪያ ለሚስተዋለው የወጥነት ችግር መፍትሄ እንዲያፈላልግ ስለተቋቋመው ግብረ-ኃይል በኢትዮጵያ የፌዴራል ጠበቆች ማህበር የተሰጠ መግለጫ

Statement by the Ethiopian Federal Lawyers Association Regarding the Task Force Established to Find Solutions to the Inconsistency in Lawyers' Tax Payment

በጠበቆች የግብር አከፋፈል ዙሪያ ለሚስተዋለው የወጥነት ችግር መፍትሄ እንዲያፈላልግ ስለተቋቋመው ግብረ-ኃይል በኢትዮጵያ የፌዴራል ጠበቆች ማህበር የተሰጠ መግለጫ

የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር ለበርካታ አመታት በጠበቆች የግብር አከፋፈል ዙሪያ የሚስተዋለውን ወጥነት የጎደለው አሠራር መፍትሄ ለመስጠት የሚያስተባበር ስራውን የሚሰራ ግብረ-ኃይል (Task Force) አቋቋመ::

የጠበቆች የታክስ አከፋፈልን በተመለከተ ከታክስ የሂሳብ መዝገብ አያያዝ; ከማሽን አጠቃቀም; ከወጪ አያያዝ እንዲሁም ጠበቆች እንደ ነጋዴ ተቆጥረው አግባብነት በሌላቸው መመሪያዎች ጭምር ከመስተናገድ አንጻር የሚስተዋሉ ተጨባጭ የወጥነት ችግሮች ቢኖሩም በዚሁ ወጥነት በሌለው የተዛባ አሠራር የግብር ክፍያ አገልግሎቱ እየተሰጠ ይገኛል፡፡ በዚህም ምክንያት ጠበቆች ለተለያዩ መጉላላቶች ሲጋለት ቆይቷል፡፡

የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማህበር በበጀት ዓመቱ ከሀምሌ ወር የመጀመሪያዎቹ ቀናት ጀምሮ ለበርካታ አመታት የዘለቀውን ይህንኑ የግብር አከፋፈል ወጥነት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት የአጭርና የረጅም ግዜ መፍትሄ እንዲገኝ ለማስቻል በማሰብ በማህበሩ የስራ ኃላፊዎች የሚመራ አስር አባላት ያሉት ግብረ-ኃይል አቋቁሞ ወደ ስራ ገብቷል::

ግብረ ሀይሉ ሀምሌ 11 ቀን 2014ዓ.ም በማህበሩ ጽ/ቤት ባደረገው ውይይት ስራው በሚመራበት የድርጊት መርሃ ግብር ላይ ተወያይቶ ወደ ስራ የገባ ሲሆን በዚህም በአባላቱና በግብር ሰብሳቢው መስሪያ ቤት ወጥ የሆነ አረዳድ ከመፍጠር ጀምሮ አማራጮችን በማቅረብ እንዲሁም ከሚመልከታቸው የመንግሥት ተቋማት ጋር ውይይቶችን በማድረግ ለአጭርና ለዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት መሰራት እንደሚገባ አቅጣጫ ተሰጥቷል::

ማህበሩ በግብረ-ኃይሉ በኩል በሚሰሩ ስራዎች የሚመጡ ውጤቶች በየ ጊዜው የሚያሳውቅ ሲሆን ጠበቆችም ተደራራቢ ኃላፊነት እንዳለበት የሙያ ማኅበረሰብ እንደየደረጃችሁ ወቅቱን ጠብቃችሁ አመታዊ የግብር ግዴታችሁን እየተወጣችሁ እንድትቆዩ ማህበሩ ለማሳሰብ ይወዳል::

የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር

Relevant Departments and People
Tagged Under: Ethiopian Federal Lawyers Association Lawyers Legal Issues Legal Professionals tax administration Tax Payment
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች