የፍትሕ ሚኒስቴር በአዋጅ ከተሰጡት ዋነኛ ተግባራት ዉስጥ አንዱ የወንጀል ሕግ አፈፃፀም ዉጤታማነትን ማሳደግ ሲሆን ተቋሙ በተጠናቀቀዉ የ2015 በጀት ዓመት ይህንኑ ተግባሩን ለማሳካት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ በመሥራት የተሻለ አፈፃፀም አስመዝግቧል፡፡
በዚሁ መሠረትም ተቋሙ የወንጀል ምርመራ መዛግብት አፈፃፀም በተመለከተ ምርመራቸው ተጠናቀው የሚቀርቡ መዝገቦችን 84% ለማጥራት አቅዶ በበጀት ዓመቱ ውስጥ በአራቱም የወንጀል ዓይነቶች ማለትም በኢኮኖሚ 2,461፣ በድንበር ተሻጋሪ 751፣ በሙስና 628፣ በልዩ ልዩ ወንጀል ጉዳዮች ደግሞ 32,894 በአጠቃላይ 36,734 የምርመራ መዝገቦች በዐቃቤያነ ሕግ እጅ የነበሩ ሲሆን ከእነዚህ መካከል በ34,643 መዛግብት ላይ ዐቃቤ ሕግ የተለያዩ ውሳኔዎችን ሰጥቷል፡፡
በመሆኑመ የምርመራ መዝገቦችን የማጥራት ምጣኔ አፈጻፀም በእቅድ ተይዞ ከነበረዉ 84% በአማካይ ወደ 94.3% በማድረስ ከተቀመጠው እቅድ በ10.3% ብልጫ ማስመዘግብ ችሏል፡፡
የምርመራ መዛገብትን የማጥራት ምጣኔ ዝርዝር አፈፃፀሙ ከስራ ክፍሎች አንፃር ሲታይ ውሳኔ እንዲሰጥባቸው ከቀረቡት መዛግብት ዉስጥ የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀል ጉዳዮች 99.7%፣ በኢኮኖሚ ነክ ወንጀሎች ጉዳዮች 93.13%፣ የልዩ ልዩ ወንጀል ጉዳዮች 94.4% እና የሙስና ወንጀል ጉዳዮች 85.8% ከእቅድ በላይ ፈፅሟል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ አፈፃፀሙ የተሻለ ቢሆንም ነገር ግን በበጀት ዓመቱ ከቀረቡ መዛግብት ዉስጥ በተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ የወንጀል ጉዳዮች 2፤ በኢኮኖሚ ነክ ወንጀል ጉዳዮች 169፤ በሙስና ወንጀል ጉዳዮች 89 እና ልዩልዩ ወንጀል ጉዳዮች 1851 መዝገቦች በአጠቃላይ 2111 መዝገቦች ደግሞ ወደ 2016 የበጀት ዓመት የተላለፉ በመሆኑ በቀጣይ ትኩረት ሰጥቶ መዛግብትን የማጥራት ስራ መሥራት እንደሚገባ በአፅንኦት ተቀምጧል፡፡