በፍትህ ሚኒስቴር በለሙ ሁለት የቴክኖሎጂ ሲስተሞች ላይ ለመካከለኛ አመራሮች ስልጠና ተሰጠ

Ministry of Justice Provides Training on Developed Technology Systems for Middle Management

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የዐቃብያነ ሕግ አስተዳደር ዋና ጉባኤ ፅ/ቤት የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች እንዲሁም የተቋሙን የደብዳቤ መለዋወጫ ሥርዓትን በቴክኖሎጂ የተደገፈ ለማድረግ ባለማቸው ሲስተሞች ላይ በዛሬው ዕለት ለተቋሙ መካከለኛ አመራሮች ሥልጠና ሰቷል፡፡

በሥልጠና መድረኩ እንደተመላከተው ከዚህ በፊት የነበረው የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የዐቃብያነ ሕግ አስተዳደር ዋና ጉባኤ ፅ/ቤት የሚሰጣቸው አገልግሎቶች እንዲሁም የተቋሙ የደብዳቤ መለዋወጫ ሥርዓት የሚመራው ለመፈፀም ሰፊ ጊዜ በሚወስዱ፣ ብዙ ምልልስ በሚጠይቁ ብሎም የሃብት ብክነት በነበረባቸው ሂደቶች እንደነበረ እና እነዚህ የለሙ ሲስተሞች ይህንን በማስቀረት በቴክኖሎጂ የተደገፈ ቀልጣፋ፣ ውጤታማ፣ተጠያቂነትና ግልፅነትን ባረጋገጠ መልኩ አገልግሎቶቹን ለመስጠት ብሎም በስራ ክፍሎች መካከል ደብዳቤዎችን መለዋወጥ ያስችላሉ ተብሏል፡፡

የዐቃብያነ ሕግ አስተዳደር ዋና ጉባኤ ፅ/ቤት የሚሰጣቸውን አገልግሎቶችን በቴክኖሎጂ ለመደገፍ የለማው HRMS (Human Resource Management System) የዐቃብያነ ሕግ ፈቃድ፣ ቅሬታ፣ የስራ መልቀቅያ፣ ዝውውር፣ የኦንላይን እና የመሳሰሉትን አገልግሎቶች የስራ ክፍል ሀላፊዎች እንዲሁም ሰራተኞች በተዘጋጀላቸው የተጠቃሚ ስምና የይለፍ ቃል መሠረት በመግባት በቀላሉ መስተናገድ የሚያስችል እና አዲስ የለማ ሲስተም ሲሆን ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ ወደ ትግበራ የሚገባ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በሌላ በኩል በተለይም የስራ ቅልጥፍናን ከፍ ከማድረጉ በተጨማሪ በተቋሙ ወረቀት አልባ የሆነ የአሠራር ሂደትን ሙሉ ለሙሉ በሚባል ሁኔታ መተግበር ለማስቻል የለማው እና ከዚህ በፊት በስራ ላይ የዋለው የLMS (Letter Management System) የደብዳቤ መለዋወጫ ሥርዓት በውስጡ የስራ ክፍሎች ዕርስ በርሳቸው የሚለዋወጧቸውን ብሎም ከሌሎች ከተቋሙ ውጪ የሚመጡ ደብዳቤዎች ለሚመለከተው የስራ ክፍል የሚላክበትን ሥርዓት በቀላሉ የዘረጋ እንደሆነ ተገልፆል፡፡

Tagged Under: HRMS • Technology Systems • Training
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች