የዐቃቤያነ ሕግ አስተዳደር ዋና ጉባኤ ጽ/ቤት

የፌደራል ዐቃቤያነ ሕግ አስተዳደር ዋና ጉባኤ ጽሕፈት ቤት በተቋም ግንባታ እና ሪፎርም ዘርፍ ስር የሚገኝ የሥራ ክፍል ሲሆን የዐቃቤያን ሕግ ስምሪትና የአሠራር ውጤታማነት ማሻሻያ ሥርዓት መቅረጽ፣ ብቃት ያላቸው ዐቃቤያነ ሕግ ለመሳብና ያሉትን ለማቆየት የሚያስችል ስትራቴጂዎችን መቅረጽ፣ የዐቃቤያነ ሕግ የስራ የምዘና ሥርዓትን ማስተዳደር፣ ከዐቃቤያነ ሕግ አስተዳደር ዋና ጉባኤ ጋር በመሆን ለተቋሙ የሚያስፈልጉ ዐቃቤያነ ሕግ የስራ መደብ አይነት፣ ብዛትና ተፈላጊ ችሎታ ሰነድ በማዘጋጀት ዐቃቤያነ ሕግ በደረጃ ዕድገት፣ በቅጥር፣ በዝውውር እንዲሟሉ ማድረግ፣ለዐቃቤያነ ሕግ አስተዳደር ዋና ጉባዔው የሬጂስትራር እና ሴክሬታሪያት አገልግሎት መስጠት፣ የዐቃቤያነ ሕግ የስራ ላይ መገኘት ሪፖርት መሰብሰብ፣ የዐቃቤያነ ሕግ አስተዳደር ዋና ጉባኤውን ውሳኔ በማይጠይቁ የዐቃቤያን ሕግ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት እና አጠቃላይ የሰው ኃይል አስተዳደርን የሚመለከቱ ተግባራትን ማከናወን ከተጣሉበት ኃላፊነቶቹ መካከል ዋና ዋናዎቹ ናቸው።

የሥራ ክፍሉን ያግኙ

የሥራ ክፍሉ መሪ

ጌታነህ ሀብታሙ ገለታ

ኃላፊ