የፍትሕ ሚኒስቴር በተባበሩት መንግስታት ሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽን ፅ/ቤት የኢኮኖሚ፣ ማህራዊ እና ባህላዊ መብቶች ተጠሪ ጋር ተወያየ

Ministry of Justice Discusses with UN Human Rights Office Representative for Economic, Social, and Cultural Rights

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር ኤርምያስ የማነብርሃን (ዶ/ር) እና በተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽን ፅ/ቤት የኢኮኖሚ፣ ማኅበራዊ እና ባህላዊ መብቶች ከፍተኛ ተጠሪ ሚስተር ፕራዲፕ ዋግል (Mr.Pradeep Wagle) በኢኮኖሚ፣ ማኅበራዊ እና ባህላዊ መብቶች ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር አድርገዋል፡፡

ዉይይታቸዉም በዋናነት ኢትየጵያ እነዚህን መብቶች ከማስከበር አንጻር እያከናወነቻቸዉ ያሉ ተግባራትን እንዲሁም መብቶቹን ከማስከበር ጋር በተያያዘ በቀጣይ ለማከናወን በዕቅድ ደረጃ በተያዙ ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ ለመሥራት በሚያስችሏቸው ሁኔታዎች ላይ ትኩረት አድርገዉ መክረዋል።

በዚህ ወቅት በፍትሕ ሚኒስቴር የተቋም ግንባታና ሪፎርም ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር ኤርሚያስ የማነብርሃን (ዶ/ር) የኢኮኖሚ፣ ማኅበራዊና ባህላዊ መብቶች እንደ ሲቪል እና ፖለቲካ መብቶች ሁሉ ለሰው ልጆች እጅግ አስፈላጊ የሆኑ መብቶች መሆናቸዉን አንስተዉ መብቶቹን ከማክበር እና ከማስከበር አንጻር የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን አስታውሰው መንግሥት ለነዚህ መብቶች መረጋገጥ የብሔራዊ ሰብዓዊ መብት ድርጊት መርሃ ግብርን እንዲሁም ለመጀመሪያ ጊዜ የንግድ እና ሰብዓዊ መብት ድርጊት መርሃ ግብር ነድፎ ተግባራዊነቱን ለመከታተል የድርጊት መርሃ ግብሮቹን በመቅረጽ ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ መርሃ ግብሮቹ ሀገሪቱ ከተባበሩት መንግስታት ሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት አባል ሀገራት የተቀበለቻቸውን ምክረ ሃሳቦች ተፈጻሚነት ለመከታተል እንደሚረዱም አክለው አንስተዋል፡፡

በዚህ ረገድ ተቋማቸው ፍትሕ ሚኒስቴር በሕግ የተጣለበትን ኃላፊነት ለመወጣት በሚያደርገው ጥረት ከተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽን ፅ/ቤት የኢኮኖሚ፣ ማህራዊ እና ባህላዊ መብቶች ስራ አመራር እና ባለሙያዎች ጋር በአቅም ግንባታ፣ በሙያዊ አበርክቶ እና በሌሎች የድግግፍ መስኮች በጋራ ለመሥራት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽን ፅ/ቤት ኢኮኖሚ፣ ማኅበራዊ እና ባህላዊ መብቶች ከፍተኛ ተጠሪ ሚስተር ፕራዲፐ ዋግሌ (Mr.Pradeep Wagle) በበኩላቸዉ በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የሰብዓዊ መብትን ከማስከበር አንጻር በጽ/ቤቱ የተደረጉትን ሙያዊ ድጋፎች በማንሳት መሰል ድጋፎችን በማድረግ ኢትዮጵያም የፈረመቻቸውን ዓለም ዐቀፍ እና አህጉራዊ ስምምነቶች የሚጥሉባትን ግዴታዎች በተሻለ እንድትወጣ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ለመሥራት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ተቋማቱ በዛሬው ውይይት ስምምነት ላይ የተደረሰባቸውን የትግግዝ መስኮች መነሻ በማድረግ በባለሙያዎች ደረጃ ተከታታይ ምክክሮችን በማካሄድ ወደ ተግባር የመለወጥ ስራ እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡

Tagged Under: action african countries and cultural rights Bilateral Cooperation Budget Capacity Building civil and political rights cultural Economic finance financial fiscal human human rights implementation Implementation international treaties Legal Reforms National national human rights action plan office plan Policy Implementation Rights social Technical Assistance un human rights office
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች

ተመሳሳይ ዜናዎች