የፍትሕ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማቱ የብሔር ብሔረሰቦች ቀንን በጋራ አከበሩ

Ministry of Justice and Affiliated Institutions Jointly Celebrate Nations, Nationalities, and Peoples' Day

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማቱ 18ኛውን የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀንን “ብዝሀነትና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን አዳራሽ አክብረዋል፡፡

በበአሉ ላይ የፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ፣ የፍትሕ ሚኒስቴር የተቋም ግንባታና ሪፎርም ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር ዶክተር ኤርሚያስ የማነብርሃን፣ የተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች እንዲሁም ባለሙያዎች ተገኝዋል።

የበአሉን ታዳሚዎች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፍት የፍትሕ ሚኒስትሩ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ በአሉን አስመልክቶ የተዘጋጀው ዝርዝር ሰነድ እንደሚቀርብና ሰፋ ያለ ውይይት እንደሚደረግበት ጠቁመው ዝግጅቱን በይፋ አስጀምረዋል።

ሕብረ ብሔራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓት እና የሰላም ግንባታ በኢትዮጵያ በሚል ርዕስ ቀኑን አስመልክቶ የተዘጋጀው የመወያያ ሰነድ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀሚድ ከኒሶ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

በውይይቱም የዘንድሮውን የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ስናከብር ለአሁናዊ ሀገራዊ ችግሮቻችን የመፍትሔ አካል መሆን እንደሚገባን ተጠቁሟል፡፡

መድረኩን በአወያይነት የመሩት የፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር ዶክተር ኤርሚያስ የማነብርሃን ፌዴራሊዝም በአለማችን በሕዝብ ብዛት፣በሀብትና በቆዳ ሰፋት ሰፊ የሆነ ሕዝብ ያላቸው አብዛኞቹ ሀገራት የሚከተሉት ሥርዓት መሆኑንና በውስጡም የጋራና የተናጠል አስተዳደር የሚባሉ ሁለት መሠረታዊ ነገሮችን እንደሚያካት ገልፀዋል።

አያይዘውም ብዝሀነታችንና አንድነታችንን በማስማማት ችግሮችን ተቋቁሞ የመፍትሄው አካል በመሆን በየተቋሞቻችን የድርሻችንን ማበርከት ይገባል ብለዋል፡፡

በመጨረሻም በቀረበው የመወያያ ሰነድ ላይ የተለያዩ አስተያየቶች እና ሃሳቦች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል፤ ለተነሱት ጥያቃዎችም ምላሽ ተሰጥቷል፡፡

የኢፌዴሪ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን፣ የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ፣ የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት፣ የፌዴራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን የፍትሕ ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋማት መሆናቸው ይታወቃል።

Tagged Under: appeals authentication civil Civil Society Organizations commission constitutionalism correctional day diversity document document authentication and registration service federal Federalism Good Governance inclusivity Legal Reform national reconciliation Nationalities Nations organizations peoples' registration Rule of Law Service society Tax unity
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች