የሚኒስትሮች ግብረ-ኃይል በሰሜናዊው የሀገራችን ክፍል በተከሰተው ግጭት አውድ ውስጥ በተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ዙሪያ እየተከናወኑ ያሉ አበይት ተግባራትን አስመልክቶ ሶስተኛውን ውይይት በዛሬው ዕለት አካሄደ

Ministers’ Task Force Holds Third Meeting on Human Rights Violations in Northern Ethiopia Conflict

የሚኒስትሮች ግብረ-ኃይል በሰሜናዊው የሀገራችን ክፍል በተከሰተው ግጭት አውድ ውስጥ በተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ዙሪያ እየተከናወኑ ያሉ አበይት ተግባራትን አስመልክቶ ሶስተኛውን ውይይት በዛሬው ዕለት አካሄደ

በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በትግራይ፣ በአማራ እና በአፋር ክልሎች በተከሰተው ግጭት አውድ ውስጥ፤ ከሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ጋር ተያይዞ የተፈጸሙ ወንጀሎችን ከማጣራት፣ ተጎጂዎችን ከመጠበቅ እና ከመደገፍ አንጻር ስራዎችን ለማስተባበር የተቋቋመው የሚኒስትሮች ግብረ-ኃይል እየተከናወኑ ያሉ አበይት ተግባራትን አስመልክቶ ሶስተኛውን ስብሰባ በዛሬው ዕለት አካሄደ፡፡

በመድረኩም የሚኒስትሮች ግብረ-ኃይል ጽ/ቤት በሁለተኛ መደበኛ ስብሰባው ላይ በተቀመጠው የስራ አቅጣጫ መሠረት የተከናወኑ ስራዎችን፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን እንዲሁም ጽ/ቤቱ ያለበትን ወቅታዊ የስራ ሁኔታ የሚያመላክት ዝርዝር ሪፖርት የግብረ-ኃይሉ ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ዶክተር ታደሰ ካሳ አቅርበዋል፡፡

በተጨማሪም ግብረ-ኃይሉ በተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እና በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ጥምር የምርመራ ቡድን፤ የሽግግር ፍትሕ አማራጭን ማጤን እና ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ በሰጡት ምክረ-ሀሳብ መሠረት ለፖሊሲ መነሻነት የሚያገለግል ረቂቅ ሰነድ ተዘጋጅቶ፤ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የሕግ ጥናት፤ ማርቀቅና ማጠቃለል ዳይሬክቶሬት ጀኔራል ዳይሬክተር የሆኑት አቶ በላይይሁን ይርጋ የሰነዱን ይዘት ለመድረኩ አቅርበዋል፡፡

በመጨረሻም የሚኒስትሮች ግብረ-ኃይሉ በቀረቡት ሪፖርትና ረቂቅ ሰነድ ላይ የተለያዩ ሀሳቦች ተነስተው ውይይቱን ካደረገ በኋላ በቀጣይ ሊወሰዱ ስለሚገባቸው እርምጃዎች አቅጣጫዎች በማስቀመጥ የዕለቱን ምክክር አጠናቀዋል፡፡

Relevant Departments and People
Tagged Under: Human Rights Violations • Northern Ethiopia Conflict
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች