በፌዴራል ደረጃ ለምስክርነት የሚቀርቡ በሰው መነገድ ወንጅል ተጎጅዎችን እና ተጎጅ ፍልሰተኞች በፍርድ ሂደት ያላቸውን ተሳትፎ ለማሻሻል በህግ አስከባሪ ተቋማት እና አገልግሎት ሰጪዎች መካከል የመግባቢያ ሰነድ ተፈረመ

Memorandum of Understanding Signed Between Law Enforcement Agencies and Service Providers to Enhance the Participation of Trafficking Victims and Migrant Victims in Federal Court Proceedings

በሰው መነገድ እና በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀሎች በዜጎች አካል እና ደኅንነት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱና ለሰብዓዊ መብት የሚያጋልጡ ከመሆናቸውም በላይ በሀገር ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሚያደርሱ መሆናቸውንና ወንጀሉን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የተጎጅ ምስክሮች ተሳትፎ እጅግ ወሳኝ ቢሆንም ለተጎጅ ምስክሮች የሚደረግ የተጠናከረ ጥበቃና ድጋፍ ባለመኖሩ ምክንያት ብዙ ተጎጅ ምስክሮች ለምስክርነት ለመቅረብ ፍላጎት እንደሌላቸው ይህም ወንጀል አድራጊዎችን ወደ ፍትሕ ከማቅረብ አንጻር አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩን እና የመግባቢያ ሰነዱ በሕግ አስፈጻሚ አካላትና በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት መካከል ያለውን ትብብር በማሳደግ ተጎጅ ምስክሮች የሚሰጣቸው ድጋፍ ሁሉን አቀፍ በሆነ መልኩ የሚያሳድግ እና በምርመራ እና በፍርድ ሂደት ደህንነታቸው ተጠብቆ ውጤታማ ተሳትፎ እንዲያደርጉ የሚያስችል መሆኑን በፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐ/ሕግ ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ የሆኑት ክቡር አቶ ፍቃዱ ፀጋ ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ዘላለም መንግስቴ በበኩላቸው ይህ የመግባቢያ ሰነድ መፈረሙ ወንጀሎቹን ከመከላከል እና ከመቆጣጠር አንጻር ብሎም የተጎጂዎችን መብት ከማስከበር አንጻር ከፍተኛ አስተዋጾ እንደሚኖረው እና ተመሳሳይ ተሞክሮ ወደ ክልሎችም መስፋፋት እንዳለበት ገልጸዋል፡፡

የመግባቢያ ሰነዱን የፈረሙት አገልግሎት ሰጪ የሆኑት ተቋማትም በመግባቢያ ሰነዱ መሠረት ተደራሽ ወጥ እና ፍትሃዊ የሆነ አገልግሎት መስጠታቸውን እና ከሕግ አስከባሪ ተቋማት ጋር በትብብር መስራታቸውን እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል፡፡

በመጨረሻም ክቡር አቶ ፈቃዱ ጸጋ የመግባቢያ ሰነዱን አተገባበር እና አፈጻጸምን በተመለከተ እያንዳንዱ ፈራሚ ተቋም በትጋት እና በትብብር መሥራት እንዳለበት እንዲሁም የፍልሰት ብሔራዊ የትብብር ጥምረት ፅ/ቤት የመግባቢያ ሰነዱ እንዲተገበር የማስተባበር ኃላፊነቱን እንዲወጣ በማሳሰብ የማጠቃለያ ሀሳብ ሰጥተዋል፡፡

Tagged Under: court Criminal Justice Cross-Border Crime enforcement federal federal police commission human Human Trafficking law Law Enforcement Legal Aid Memorandum of Understanding migrant Migrant Smuggling Police protection providers Security Service service providers Smuggling trafficking trafficking victims victim Victim protection witness Witness Protection
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች

ተመሳሳይ ዜናዎች