ሟችን ከገደሉ በኋላ ከ670 ሺ ብር በላይ የሚያወጡ ጂ.ኤስ.አይ የተባለን ድርጅት ንብረቶች ይዘው ሲወጡ እጅ ከፍንጅ የተያዙ ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ

Individuals Caught Red-Handed Stealing Assets Worth Over 670,000 Birr from GSI After Murdering Victim Sentenced to Prison

በዐቃቤ ሕግ የክስ መዝገብ ላይ 1ኛ ዳኛቸው አንዱበር፣ 2ኛ ሸፈራው አስፋው የተባሉ ሁለት ተከሳሾች በ2 ክሶች ተከሰዋል፡፡

በ1ኛ ክስ ላይ ተከሳሾች ሰውን ለመግደል አስበው መስከረም 29 ቀን 2015 ዓ.ም ከምሽቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ኖህ ፕላዛ 4ኛ ፎቅ ጂ.ኤስ.አይ በተባለው መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ውስጥ ከሚገኘው የድርጅቱ የዕቃ ማከማቻ ክፍል ውስጥ ሟች ጥላሁን አለማየሁን ሁለቱም ተከሳሾች በቢለዋ ሆዱ ላይ በመውጋትና አንገቱን በእጃቸው በማነቅ ጉዳት እንዲደርስበት ካደረጉ በኋላ በ2ኛ ክስ የተጠቀሰውን ንብረት በመያዝ 1ኛ ተከሳሽ የድርጅቱ ጥበቃ መሆኑን እንደምቹ ሁኔታ በመጠቀም ለማምለጥ ሲሞክሩ በጊዜው የድርጅቱን ግቢ ሲጠብቁ በነበሩ ግለሰቦች አማካኝነት በፖሊስ ሲያዙ ሟችም በስለት መሳሪያ ሆዱ ላይ በመወጋቱ ጉዳት ስለደረሰበት እና በሌላ ሰው እጅ አንገቱን በመታነቁ ምክንያት ህይወቱ ያለፈ በመሆኑ በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን በፈፀሙት የሰው ግድያ ወንጀል ተከሰዋል፡፡

በተመሳሳይ በ2ኛ ክሳቸው ላይ ተከሳሾች የማይገባቸውን ብልጽግና ለራሳቸው ለማግኘት በማሰብ ከላይ በ1ኛ ክስ ላይ በተጠቀሰው ቀን፣ ሰዓት፣ ቦታ እና ሁኔታ ሟችን ከገደሉ በኋላ 1ኛ ተከሳሽ ተቀጥሮ ጥበቃ ሆኖ የሚሰራበት ጂ.ኤስ.አይ የተባለው መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ንብረት የሆኑትን መለያቸው ሳምሰንግ ኤ 21 ኤስ ብዛታቸው 35 የሆነና የዋጋ ግምታቸው ደግሞ 670 ሺ 909 ብር ከ24 ሳንቲም የሚያወጡትን 1ኛ ተከሳሽ በጥቁር ቦርሳ ተሸክሞ ሊወጡ ሲሉ እጅ ከፍንጅ የተያዙ በመሆኑ በፈጸሙት በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን የከባድ ስርቆት ወንጀል የተከሰሱ በመሆኑ በፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ የልዩ ልዩ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ ክስ አቅርቦባቸው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ ወንጀል ችሎት ክርክር ሲደረግ ቆይቷል፡፡

በክርክሩ ሂደትም የዐቃቤ ሕግ ማስረጃ ከተሰማ በኋላ ተከሳሾች እንዲከላከሉ ብይን ተሰጥቶ ተከሳሾች የመከላከያ ምስክር አቅርበው ያሰሙ ቢሆንም በዐቃቤ ሕግ የቀረበባቸውን ክስ መከላከል ባለመቻላቸው ምክንያት ፍርድ ቤቱ በተከሳሾች ላይ የጥፋተኛነት ፍርድ በመስጠት የቅጣት ውሳኔ በማሳረፍ 1ኛ ተከሳሽ በ12 ዓመት እና 2ኛ ተከሳሽ በ10 ዓመት እስራት እንዲቀጡ ሲል ወስኗል፡፡

Tagged Under: Asset Seizure bole sub-city case conviction court criminal Criminal Case district embezzlement federal Federal High Court felony grand grand larceny high Homicide imprisonment larceny lideta lideta district manslaughter Murder prison sentence Robbery samsung Theft
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች