የ2016 10 ወራት የማክሮ ኢኮኖሚና የዘርፎች ዋና ዋና አፈፃፀም እና የ2017 የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ ዉይይት ተካሄደ

Discussion Held on the 10-Month Macroeconomic and Sectoral Key Performances of 2016 and the Focus Areas of 2017

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር በ2016 ዓ.ም ዋና ዋና ሀገራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ አፈፃፀምና የ2017 የትኩረት አቅጣጫዎች እንዲሁም በ2017 የበጀት ዓመት በትኩረት ሊተገበሩ የሚገባቸዉ ጉዳዮች ዙሪያ በዛሬዉ እለት ዉይይት ተካሂዷል፡፡

በዉይይቱ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስን ጨምሮ ሚኒስትር ዲኤታዎች እና የተቋሙ መካከለኛ አመራሮች ተሳትፈዉበታል፡፡

በተለይም ከሀገራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ ጋር በተያያዘ ሁሉም ተቋማት በቂ ግንዛቤ ኑሯቸዉ ስራቸዉን ቢተገብሩ በሚያደርጉት የስራ እንቅስቃሴ አጋዥ እንደሚሆንና እንደ ፍትሕ ሚኒስቴርም በተለይም ጉዳዩ የሚመለከታቸዉ የኢኮኖሚ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬትና መሰል ዳይሬክቶሬቶች አገራዊ ማክሮ ኢኮኖሚ ግንዛቤ ለስራቸዉ አጋዥ እንደሚሆናቸዉ የፍትሕ ሚኒስትሩ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ ተናግረዋል፡፡

ቀጥሎም ዋና ዋና ሀገራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ አፈፃፀምና ያተኮረባቻው ስድስት ዋና ዋና ነጥቦች ማለትም ዓለማቀፋዊ የኢኮኖሚ አዝማሚያ እና ሀገራዊ አፈፃፀም፣ ዋና ዋና የኢኮኖሚ ዕድገት ምንጮች አፈፃፀምወ ፣ የመሰረተ ልማት እና የፕሮጀክቶች አፈፃፀም ፣ የማኅበራዊ ዘርፍ አፈፃፀም፣ የአሰተዳደር ዘርፎች አፈፃፀም እንዲሁም የቀጣይ የ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎች በፍትሕ ሚኒስቴር የተቋም ግንባታና የሪፎርም ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር ዶ/ር ኤርሚያስ የማነብርሃን በዝርዝር የቀርበ ሲሆን የዉይይቱ ተሳታፊዎችም አስተያየታቸዉንና ጥያቄዎችን ያነሱ ሲሆን በተቋሙ የበላይ አመራሮች ምላሽ ተሰጥቶባቸዉና የቀጣይ የስራ አቅጣጫዎች ተመላክተዉ ዉይይቱ ተጠናቋል፡፡

Tagged Under: 2016 2017 2017 budget areas Budget budgetary allocation Economic economic growth economic reforms ermias ermias yemaneberhan gideon gideon timotheos growth Infrastructure Development macroeconomic national development plan performance Policy discussion Public Administration review sectoral sectoral performance timotheos yemaneberhan
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች

ተመሳሳይ ዜናዎች

No data was found