ሰፌድ ወሰደብኝ በሚል በተፈጠረ አለመግባባት ሟችን የገደሉ ተከሳሾች በጽኑ እስራት ተቀጡ

Defendants Sentenced to Lengthy Imprisonment for Fatally Assaulting Victim Over a Dispute About Shard

በዐቃቤ ሕግ የክስ መዝገብ ላይ 1ኛ ቢምረው(አንዱአለም) አለሙ ይግዛው፣ 2ኛ አቤው(መኮንን) ያለው ፈለቀ የተባሉ ተከሳሾች ግንቦት 12 ቀን 2014 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ሲሆን በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 ቄስ ሰፈር እየተባለ ከሚጠራው አካባቢ ግንቦት 11 ቀን 2014 ዓ.ም ሰፌድ ወሰደብኝ በሚል በአንድ የዐቃቤ ሕግ ምስክር እና በተከሳሾች መሀል አለመግባባት ተፈጠሮ፣ ይሄን አለመግባባት በእርቅ ለመጨረስ በሂደት ላይ እያለ ተጠርጣሪዎች ዱላ፣ አካፋ እና ድንጋይ በመያዝ ወደ አንደኛው የዐቃቤ ሕግ ምስክር የስራ ቦታ በመሄድ ቤቱ ላይ ድንጋይ በመወርወር እንዲወጡ ካደረጉ በኋላ ጨካኝነታቸውን እና ነውረኝነታቸውን በሚያሳይ ሁኔታ 1ኛ ተከሳሽ ድንጋይ ወርውሮ ሟች አወቀ መቆየቴን ቅንድቡን ሲመታው 2ኛ ተከሳሽ በአካፋ ማጅራቱን መቶ በመጣል ህይወቱ እንዲያልፍ ያደረጉ በመሆኑ በፈፀሙት በዋና ወንጀል አድራጊነት ከባድ የሰው መግደል ወንጀል በፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ የልዩ ልዩ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ ክስ አቅርቦባቸው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ ግድያና ከባድ ውንብድና ወንጀል ችሎት ክርክር ሲደረግ ቆይቷል፡፡

በክርክሩ ሂደትም 1ኛ ተከሳሽ በማረሚያ ቤት ሆኖ፣ 2ኛ ተከሳሽ በሌለበት ጉዳዩ እንዲቀጥል ተወስኖ የዐቃቤ ሕግ ማስረጃ ከተሰማ በኋላ ተከሳሾች እንዲከላከሉ ብይን ተሰጥቶ 1ኛ ተከሳሽ የመከላከያ ምስክር አቅርቦ ያሰማ ቢሆንም በዐቃቤ ሕግ የቀረበበትን ክስ መከላከል ባለመቻሉ፣ 2ኛ ተከሳሽም የመከላከያ ምስክር ባለማቅረቡ ፍርድ ቤቱ በተከሳሾች ላይ የጥፋተኛነት ፍርድ በመስጠት የቅጣት ውሳኔ በማሳረፍ በ1ኛ ተከሳሽ ላይ በ12 ዓመት ጽኑ እስራት እና በ2ኛ ተከሳሽ ላይ በሌለበት በ20 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ሲል ወስኗል፡፡

Tagged Under: assault • attorney • capital punishment • case • convict • conviction • court • criminal • Criminal Case • deadly weapon • defendant • dispute • district • federal • Federal High Court • felony • high • Homicide • imprisonment • legal counsel • lideta • lideta district • manslaughter • Murder • Prosecution • Prosecutor • severe punishment • witness testimony
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች