ዮሐንስ አሰፋ የተባለ ግለሰብን በጭካኔ የገደለው ተከሳሽ በፅኑ እስራት ተቀጣ

Defendant Who Brutally Killed Yohannes Assefa Sentenced to Rigorous Imprisonment

ዳዊት ታደለ የተባለው ተከሳሽ ሰውን ለመግደል በማሰብ ሀምሌ 25 ቀን 2014 ዓ.ም በግምት ከረፋዱ 5፡30 አካባቢ በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ጥይት ፋብሪካ አካባቢ በሚገኘው ቅድስት ማርያም ዩኒርስቲ G-01 የመማሪያ ክፍል ውስጥ ጨካኝነቱንና አደገኛነቱን በሚያሳይ መልኩ ሟች ዮሐንስ አሰፋን እጁን ደም እንዳይነካው ጓንት በማድረግ በቢላ የተለያዩ የሰውነት ክፍሎቹን በመውጋት ስለታማ በሆነ ቁስ አካል በደረሰበት ጉዳት ህይወቱ እንዲያልፍ ያደረገ በመሆኑ በፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ የልዩ ልዩ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ በ1996 ዓ.ም በወጣው የወንጀል ሕግ አንቀጽ 539/1/ሀ/ መሠረት በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ሰው ግድያና ከባድ ውንብድና ወንጀል ችሎት በፈፀመው ከባድ የሰው መግደል ወንጀል ክስ ቀርቦበት ክርክር ሲደረግ ቆይቷል፡፡

በክርክሩ ሂደትም የዐቃቤ ሕግ ማስረጃ ከተሰማ በኋላ ተከሳሽ እንዲከላከል ብይን ተሰጥቶት ተከሳሽ የመከላከያ ምስክር አቅርቦ ያሰማ ቢሆንም በዐቃቤ ሕግ የቀረበበትን ክስ መከላከል ባለመቻሉ ምክንያት ፍርድ ቤቱ በተከሳሽ ላይ የጥፋተኛነት ፍርድ በመስጠት የቅጣት ውሳኔ በማሳረፍ በ16 ዓመት ከ10 ወር ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ሲል ወስኗል፡፡

Tagged Under: addis ababa • article 539/1/a • assefa • capital punishment • conviction • court • criminal code 1996 • deadly weapon • district • federal • Federal High Court • felony • high • Homicide • imprisonment • knife • lideta • lideta district • Murder • rigorous • Rigorous Imprisonment • Sentencing
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች