ሟችን ሆን ብሎ በመተናኮስ የገደለው ተከሳሽ ጽኑ እስራት ተፈረደበት

Defendant Sentenced to Rigorous Imprisonment for Intentionally Provoking and Killing Victim

ታምራት ሲሳይ የተባለው ተከሳሽ ሰውን ለመግደል ሆን ብሎ በማሰብ ነሀሴ 22 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ በግምት 5፡15 ሰዓት ሲሆን በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 ንግስት አስፋው ሆቴል ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ሟች በሱፍቃድ ቶሎሳን እየተተናኮለ፣ ነገር እየፈለገው ቆይቶ እስኪ አንተ ወንድ ነህ በለኝ በማለት በተደጋጋሚ ሟችን ሲያስጨንቅ፤ ሟች እስኪ አንተ ወንድ ነህ በማለት ሲመልስለት ተከሳሽ ይዞት የነበረውን ቢላ ከሱሪው ውስጥ በማውጣት ሟች በተቀመጠበት በቀኝ በኩል ትክሻው ላይ በመውጋት በደረሰበት ጉዳት በህክምና እየተረዳ እያለ በእለቱ ህይወቱ ያለፈ በመሆኑ በፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ የልዩ ልዩ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ በ1996 ዓ.ም በወጣው የወንጀል ሕግ አንቀጽ 540 መሠረት በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ ግድያና ከባድ ውንብድና ወንጀል ችሎት በፈፀመው ተራ የሰው መግደል ወንጀል ክስ ቀርቦበት ክርክር ሲደረግ ቆይቷል፡፡

በክርክሩ ሂደትም የዐቃቤ ሕግ ማስረጃ ከተሰማ በኋላ ተከሳሽ እንዲከላከል ብይን ተሰጥቶ ተከሳሽ የመከላከያ ምስክር አቅርቦ ያሰማ ቢሆንም በዐቃቤ ሕግ የቀረበበትን ክስ መከላከል ባለመቻሉ ምክንያት ፍርድ ቤቱ በተከሳሽ ላይ የጥፋተኛነት ፍርድ በመስጠት የቅጣት ውሳኔ በማሳረፍ በ11 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል፡፡

Tagged Under: 1996 criminal code • article 540 • assault • conviction • court • Criminal Code • Criminal Prosecution • deadly weapon • district • federal • Federal High Court • high • Homicide • imprisonment • intentional • intentional homicide • knife • lideta • lideta district court • manslaughter • Murder • murder conviction • nefas silk lafto sub-city • rigorous • Rigorous Imprisonment
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች