ከሟች ጋር በነበራቸው ጸብ ምክንያት ቂም በመያዝ ደብድቦ የገደለው ተከሳሽ በጽኑ እስራት ተቀጣ

Defendant Sentenced to Rigorous Imprisonment for Fatally Beating Victim Out of Revenge Following Dispute

ያሬድ ሰለሞን የተባለው ተከሳሽ ሰውን ለመግደል አስቦ ሰኔ 19 ቀን 2014 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ሲሆን በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 አንቆርጫ ዳንሴ ሰፈር ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ከሟች ጉታ ከበደ ጋር በመሬት ጉዳይ በነበራቸው ጸብ ምክንያት ቂም በመያዝ በከዘራ ዱላ ከኋላ ጭንቅላቱን ደጋግሞ በመምታት ኮብልስቶን ንጣፍ ላይ እንዲወድቅ በማድረግ የራስ ቅሉ አጥንት እንዲሰበር በማድረጉ በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ህይወቱ ያለፈ በመሆኑ በፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ የልዩ ልዩ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ በ1996 ዓ.ም በወጣው የወንጀል ሕግ አንቀጽ 539/1/ሀ/ መሠረት በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ ግድያና ከባድ ውንብድና ወንጀል ችሎት በከባድ ሰው መግደል ወንጀል ክስ ቀርቦበት ክርክር ሲደረግ ቆይቷል፡፡

በክርክሩ ሂደትም የዐቃቤ ሕግ ማስረጃ ከተሰማ በኋላ ተከሳሽ እንዲከላከል ብይን ተሰጥቶ ተከሳሽ የመከላከያ ምስክር አቅርቦ ያሰማ ቢሆንም በዐቃቤ ሕግ የቀረበበትን ክስ መከላከል ባለመቻሉ ምክንያት ፍርድ ቤቱ በተከሳሽ ላይ የጥፋተኛነት ፍርድ በመስጠትና የቅጣት ውሳኔ በማሳረፍ በ14 ዓመት ከ3 ወር ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ሲል ወስኗል፡፡

Tagged Under: 1996 • article • article 539/1/a • code • conviction • court • criminal • criminal code 1996 • district • federal • Federal High Court • federal supreme court • high • Homicide • imprisonment • imprisonment sentence • lideta • lideta district court • manslaughter • Murder • revenge killing • rigorous • Rigorous Imprisonment • yeka sub-city
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች