ሟችን አንገቱን አንቆ በመያዝ ባደረሰበት ጉዳት ምክንያት ህይወቱ እንዲያልፍ ያደረገው ተከሳሽ በፅኑ እስራት ተቀጣ

Defendant Sentenced to Rigorous Imprisonment for Causing Death by Strangulation

አጥናፉ እሸቴ የተባለው ተከሳሽ ሰውን ለመግደል በማሰብ መስከረም 14 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ በግምት 10፡00 ሰዓት ሲሆን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ሙሉ ሸዋ ስጋ ቤት ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ተከሳሽ ሟች ታመነ ክፈተውን በመሳደቡ በተነሳ ፀብ ሟችን አንገቱን አንቆ በመያዝ በደረሰበት ጉዳት ምክንያት ህይወቱ በእለቱ እንዲያልፍ ያደረገ በመሆኑ በፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ የልዩ ልዩ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ሰው ግድያና ከባድ ውንብድና ወንጀል ችሎት በፈፀመው ተራ ሰው መግደል ወንጀል ክስ አቅርቦበት ክርክር ሲደረግ ቆይቷል፡፡

በክርክሩ ሂደትም የዐቃቤ ሕግ ማስረጃ ከተሰማ በኋላ ተከሳሽ እንዲከላከል ብይን ተሰጥቶ የመከላከያ ምስክሮችን በማቅረብ ያሰማ ቢሆንም የቀረበበትን ክስ ሊከላከል ባለመቻሉ ፍርድ ቤቱ በተከሳሽ ላይ የጥፋተኛነት ፍርድ በመስጠት በ7 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ሲል ወስኗል፡፡

Tagged Under: ababa • addis • addis ababa • Attempted Murder • capital punishment • case • conviction • court • criminal • Criminal Case • district • federal • Federal High Court • felony • high • Homicide • imprisonment • intentional homicide • legal case • lideta • lideta district • manslaughter • Murder • rigorous • Rigorous Imprisonment • strangulation
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች