በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር በንቃተ ሕግ ትምህርት እና ስልጠና ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት በፎረንሲክ ምርመራ እንዲሁም የDNA ትንታኔ እና የአስክሬን ምርመራ ማስረጃ አጠቃቀም ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና ለተቋሙ ዐቃቢያነ ሕግ በመሰጠት ላይ ነው፡፡
ስልጠናው በዋናነት የፎረንሲክ ምርመራ ምንነት፣ የማስረጃ አሰባሰብ እና አጠቃቀም በተለይም በግድያ እና ሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ላይ እንዴት ጥቅምላይ እንደሚውል እንዲሁም የፎረንሲክ እና የDNA ምርመራን እንዴት በማስረጃነት እንጠቀማለን? በሚሉ እና መሰል ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ውይይት ከማድረግ ባሻገር ልምድ ልውውጥ ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ ተመላክቷል፡፡
በልዩ የክረምት ስልጠና ፐሮግራም ከአሁን በፊት በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች 7 ስልጠናዎች የተሰጡ ሲሆን ይህ 8ኛው እና የመጨረሻው ስልጠና እንደሆነ ተገልጿል፡፡ ስልጠናው ለሶስት ተከታታይ ቀናት እንደሚሰጥም ተጠቁሟል፡፡