"የኢትዮጵያ የህግ ፍልስፍና" በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ ያተኮረ ወርሃዊ የፓናል ውይይት ተካሄደ

A monthly panel discussion focused on the topic 'Ethiopian Legal Philosophy' was held.

በፍትሕ ሚኒስቴር የንቃተ ህግ ትምህርትና ሥልጠና ዳሬክቶሬት አስተባባሪነት የተዘጋጀና አበይት ትኩረቱን “በኢትዮጵያ የህግ ፍልስፍና” ላይ ያደረገው 9ኛው ወርኀዊ የፓናል ውይይት ተካሂዷል፡፡

ላለፉት 9 ወራት እየተካሄደ የሚገኘው የውይይት መድረክ አላማ ከመደበኛው የስራ አውድ ወጣ ብሎ የማሰብ፣ የመነጋገርና የመከራከር ባህልን ለማሳደግ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን፤ በመስከረም ወር የተደረገው ውይይትም ከኢትዮጵያ የህግ ፍልስፍናዎች ጋር የተያያዘ መሆኑ ጉዳዩን የበለጠ ከሚከናወነው ስራ ጋር አቀራርቦ በማየት ሀሳብን በማንሸራሸር በርዕሰ ጉዳዩ ላይ ተቀራራቢ የሆነ ምልከታ ለመያዝ የሚቻልበትን እድል ለመፍጠር የሚያስችል መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

“በኢትዮጵያ የህግ ፍልስፍና” ላይ በመምህርነትና በምርምር የሚሰሩ የህግ ባለሙያ አማካኘነት ለውይይት በቀረበው መነሻ ሀሳብ ላይ እንደተመለከተው ኢትዮጵያዊ የሚባሉ ፍልስፍናዎች በሚል በተደረገው ገለፃ መሰረት ኢትዮጵያዊ ፍልስፍና በአንድ በኩል አፍሪካዊ ማንነቱ በጸረ ቅኝ አገዛዝ ፍልስፍና ፣ የብሄር እና ማህበረሰብ ፍልስፍና እንዲሁም የሀገር ሽማግሌዎች ፍልስፍና በሚባሉ የህልውና አውታሮች ላይ የተመሰረተና በዚህም ዘመናዊ የኢትዮጵያን ፍልስፍና ካስጀመረ ዘርያዕቆብ ከማህበረሰብ ፈላስፎች ደግሞ እንደ ገዳ ስርዓት ቤካ እና መሰል ጉዳዮች፤ እንዲሁም በሶስተኛው አውታር አለም አለማቀፋዊነቱ ተነስተው ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

“በኢትዮጵያ የህግ ፍልስፍና”ን በሚመለከት የኢትዮጵያ ፍልስፍና ንዑስ አካል እንደ መሆኑ በሶስትዮሽ አውታር የተመሰረተ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በዚህም የሚወጡ ህጎች በአፍሪካዊነት፣ በኢትዮጵያዊነት እና ዓለም አቀፋዊነት ውህድ የተዋሀዱ መሆናቸው ተመልክቶ በመሰረታዊነት የኢትዮጵያ ብቻ የሚባሉ ህጎች የሌሉን በመሆኑና ሁሉም ህጎቻችን ከኢትዮጵያዊነትና ከዓለም አቀፋዊነት የተቀዱ መሆናቸው ተገልፆ ምን አልባት አዲሱ “የመደመር” እሳቤ ለወደፊቱ ሀገር በቀል የህግ ፍልስፍና የሚሆንበትን መንገድ ሊከፍት የሚችልበት አጋጣሚ ለኖር እንደሚችል ተመላክቷል፡፡ ቀጠሎ በሚመጣው የአገረ-መንግስት ግንባታ ውስጥ ሶስቱን አውታሮች እያዋሀድን የህግ ፍልስፍናችንን መገንባት የሚጠበቅ መሆኑ የተመለከ ሲሆን፤ እነዚህ አውታሮች ሲዋሀዱም ብሔራዊ ጥቅምን (national interest) ፣ ኢትዮጵያዊ ባህልን (Ethiopian culture) እንዲሁም ልማትን (Development) ታሳቢ ማድረግ እንደሚገባ ተመልክቷል፡፡

በመጨረሻም ከመድረኩ በቀረበው ሀሳብ ላይ በተሳታፊዎች ሰፊ ውይይት ተደርጎ የጋራ መግባባት ከተፈጠረ በኋላ ዝግጅቱ ተጠናቋል፡፡

Tagged Under: act • african charter on the rights and welfare of the child • Capital • court • culture • decree • development • Discussion • finance • ilo • interest • Investment • judge • judicial • judiciary • law • legal • legislation • National • national interest • panel • panel discussion • Policy • proclamation • Regulation • res • statute • tribunal • Use • used
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች