በሕገ-መንግሥቱ እና በሌሎች የታክስ ሕጐች በፌዴራሉ መንግሥት እንዲሰበሰቡ የተወሰኑ የታክስ ገቢዎች ምንጫቸውም ሆነ ሥርጭታቸው በሁሉም የአገሪቱ ክልሎች የሚገኙ በመሆኑና የነዚህ ገቢዎች አሰባሰብ በብቃት መከናወን ያለበት በመሆኑ፤
በገቢ ባለሥልጣኑ የሚከናወነው ተግባርና የተለየ የሥራ ባህሪይ የሚጠይቀውን ከሙስና ምዝበራና ጉቦኝነት የፀዱና በከፍተኛ ዲሲፕሊንና ሥነ ምግባር የሚመሩበት የሠራተኞች አስተዳደር ሥርዓት ለመዘርጋት እንዲቻል፤
ይህን ኃላፊነት በብቃት እንዲወጣ የተሟላ ድርጅታዊ አቋም፣ የሰለጠነ የሰው ኃይል፣ በዘመናዊ የመረጃ ቴክኖሎጂ የሚታገዝ ቀልጣፋ የአሰራር ሥርዓት እንዲኖረው ለማስቻል የፌዴራል አገር ውስጥ ገቢ ባለሥልጣንን እንደገና ማቋቋም በማስፈለጉ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ(1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል።
•
•
•
•
•
•
•