በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የሕዝብን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ያወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 6/2015ን ለማፅደቅ የወጣ አዋጅ፤
የሕዝብን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ የወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 6/2015 ሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም በሚኒስትሮች ምክር ቤት የታወጀ መሆኑን፤
ይህንኑ በሚኒስትሮች ምክር ቤት የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 23 ንዑስ አንቀጽ (2)(ለ) መሠረት በ15 ቀናት ውስጥ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቅረብ ያለበት መሆኑን፤
የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም ነሐሴ 8 ቀን 2015 ዓ.ም ባካሄደው 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባ የመረመረውና በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 93 (3) መሠረት ያፀደቀው መሆኑን፤
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግስት አንቀጽ 23 ንዑስ አንቀጽ (2)(ለ) እና አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ (8) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•
•