ህብረተሰቡ በሚኖርበት፣ በሚማርበትና በሚሰራ በት አካባቢ በስፖርት እንቅስቃሴ ተሳታፊ የሚሆንበትን ሁኔታ ማመቻቸትና ለዚህም ዓላማ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እንዲስፋፉና እንዲጠበቁ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ፤
የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች በየአካባቢው በብዛትና በጥራት መኖር የህብረተሰቡን በተለይም የወጣቱን ጤንነት ለመጠበቅ፣ አካል ለመገንባት፣ አዕምሮ ለማበልፀግ እና ለሀገር እድገት አስተዋፆ እንዲያበረክቱ የሚያስችል በመሆኑ፤
ስፖርት ለታሰበለት ዓላማና ግብ እንዲውል ደረጃቸውን የጠበቁ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች የሚቋቋሙበትን፣ የሚተዳደሩበትን፣ ቁጥጥር የሚደረግበትን እና ሕጋዊ ጥበቃ የሚያገኙበትን ሁኔታ የሚደነግግ ሕግ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55 (1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•
•
•
•
•
•
•