የተሻረ

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የተሻሻለው ቻርተር አዋጅ

ቀይ መስቀል በዘር፣ በቀለም፣ በዜግነት፣በጾታ፣በሃይማኖት፣ በፖለቲካ አመለካከት ወይም በማናቸውም ሌላ ሁኔታ ልዩነት ሳያደርግ በጦር ሜዳ ለሚቆስሉና ለሚጐዱ በአጠቃላይ በተፈጥሮና ሰው ሠራሽ አደጋዎች ለሚጠቁ ሰዎች ተፈላጊውን ሰብአዊ ዕርዳታ በፍጥነት የሚሰጥና በሰዎች ዘንድ መግባባት ፡ መተባበር ወዳጅ ነትና ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን የሚጥር ዓለምአቀፍ እንቅስቃሴ በመሆኑ፡

የዚህ እንቅስቃሴ አካል የሆነውና በ1927ዓም የተመሠ ረተው የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር በመንግሥትና በኅብረ ተሰቡ በተለይም በአባላቱ ጠንካራ ድጋፍ በመዋቅር ስፋትም ሆነ በአገልግሎት አቅርቦት እያደገ መምጣቱን በመገንዘብ ፤

ማኅበሩ በአደጋዎች ለተጐዱ ሰዎች እርዳታ ከማቅረቡም በተጨማሪ በሃገሪቱ የልማት ሥራዎች ከሚመለከታቸው መሥሪያ ቤቶች ጋር በመተባበር የሚያደርገው ተሳትፎ እንዲሁም ዝቅተኛ የሆነውን የሕዝቡን የኑሮ ደረጃ በአነስተኛና በመሠረታዊ መመዘ ኛዎች ተቀባይነት ወደአለው ደረጃ ለማሸጋገር ለሚደረገው ጥረት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ሊበረታታ የሚገባው በመሆኑ ፤

ከአካባቢያዊ አየር ሚዛን መናጋትና ከተፈጥሮ ሃብቶች መራቆት ጋር በተዛመደ መልክ የሚከሰቱትን የድርቅና የረሃብ አደጋዎች በመከላከሉ ጥረት የሚያደርገው አስተዋጽኦ ተገቢና አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፡

ማኅበሩ ዓላማውንና ተልዕኮውን ለማሳካትና ዓለምአቀፍ ግዴታውን በነባራዊ ሁኔታዎች ላይ ተመስርቶ ለመወጣት እንዲችል አደረጃጀቱን ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አደረጃጀት አንጻር እንደገና በማዋቀር በየክልሉ እንዲ ደራጅ ማድረግ በማስፈለጉ ፡

የማኅበሩ ጠቅላላ ጉባዔ በመንግሥት ምክር ቤት ልዩ ድንጋጌ ቁጥር 21/1982 ተሻሽሎ የነበረው የማኅበሩ ቻርተር እንደገና እንዲሻሻል ያቀረበውን ጥያቄ በመቀበል ፤

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገመን ግሥት አንቀጽ 55(1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ።

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መለያ: አዋጅ ቁጥር 153/1991
ቀን: የካቲት 2፥ 1991 ዓ.ም.
Law Type: Proclamations

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች

አዋጅ ቁጥር 1379/2017

ግንቦት 14፥2017 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
አዋጅ ቁጥር 1067/2010

ጥር 18፥ 2010 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ