ለሞጆ-ሀዋሳ የፍጥነት መንገድ አርሲ ነገሌ-ሀዋሳ ክፍል) ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል መጠኑ 171 ሚሊዮን 80 ሺህ 400 የአሜሪካን ዶላር (አንድ መቶ ሰባ አንድ ሚሊዮን ሰማንያ ሺህ አራት መቶ የአሜሪካን ዶላር) የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት እና በቻይና ኤክስፖርት-ኢምፖርት መካከል ባንክ ግንቦት 4 ቀን 2009 ዓ.ም በቤጂንግ የተፈረመ በመሆኑ፤
ይህንኑ የብድር ስምምነት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኔ 28 ቀን 2009 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ያፀደቀው ስለሆነ፤
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግስት አንቀፅ 55 (1) እና (12) መሰረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•
•
•
•
•
•
•
•
•