በአገልግሎት ላይ

ስለ ዕፅዋት አዳቃይ መብት የወጣ አዋጅ

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት ዜጎች የግል ንብረት ባለቤት የመሆን መብት እንዳላቸው ስለሚደነግግና የዕፅዋት አዳቃይ መብት በዚህ ክፍል ውስጥ የሚስተናገድ ሆኖ በመገኘቱ፤

እንዲሁም አዳዲስ ዝርያዎችን ከውጭ በማስገባት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ ሲባል ዝርያውን ያፈለቁ ባለሃብቶች ከዝርያቸው ተጠቃሚ መሆን ስለሚገባቸው፤

ከዘርፉ የሚገኘውን ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ለማሳደግ የዕፅዋት አዳቃይ መብትን ከዓለም አቀፍ አሠራር ጋር በማጣጣም ዋስትና እንዲያገኝ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ፤ ከአዳቃይ የምርምር ግኝት መጠበቅ ጋር ተያይዞ የሚነሳውን አለመግባባት ለመፍታት ግልፅነትና ተጠያቂነት ያለበት የአሠራር ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ፤

የዕዕዋት አዳቃይ መብትን ከማበረታታት ጎን ለጎን አዳዲስ የዕፅዋት ዝርያን ለማውጣት ግብዓት የሆነውን የዕፅዋት ብዝሀ-ህይወት ሀብት ከዚህ ቀደም የጠበቁትን፣ አሁን እየጠበቁ ያሉትንና ወደፊትም የሚጠብቁትን በአገራችን አርሶ አደሮችና ከፊል አርብቶ አደሮች ለዘመናት የቆየውን የዕፅዋት ዘር የማቆየት፣ የመጠበቅና የማስተላለፍ ባህላዊ የማኅበረሰብ ዕውቀት እና ልማድ እንዲቀጥል ማድረግ አስፈላጊና ተገቢ በመሆኑ፤

ከዕዕዋት አዳቃይ ጋር ተያያዢነት ያላቸውን መብቶች፣ ክልከላዎችና ኃላፊነቶች ለመመዝገብ የሚያስችል የሕግ ማዕቀፍ በማውጣት የአዳቃዩን አስተዋጽኦ ማሳደግ በማስፈለጉ፤

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55 (1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል።

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መለያ: አዋጅ ቁጥር 1068/2010
ቀን: የካቲት 22፥ 2010 ዓ.ም.
Law Type: Proclamations

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች

አዋጅ ቁጥር 1288/2015

•

ሐምሌ 17፥ 2015 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
አዋጅ ቁጥር 1289/2015

•

ሰኔ 29፥ 2015 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
ደንብ ቁጥር 527/2015

•

ታኅሣሥ 4፥ 2015 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
ደንብ ቁጥር 509/2014

•

ሚያዝያ 15፥ 2014 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
ደንብ ቁጥር 465/2012

•

መጋቢት 18፥ 2012 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ