የተሻረ

የብሔራዊ የግብርና ግብአት ባለስልጣን ማቋቋሚያ አዋጅ

ለሀገሪቱ ዕድገትና ልማት መሠረት የሆነውን የግብርናውን ክፍለ ኢኮኖሚ ምርትና ምርታማነት በማሳደግ ፣ አርሶ አደሩና አርብቶ አደሩ ከዚሁ ተጠቃሚ መሆኑን ማረጋገጥ አስፈላጊ በመሆኑ ፤

የግብርናውን ዘርፍ ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ የተለያዩ የግብርና ግብዓቶችን በጥራት ፣ በዓይነትና በበቂ መጠን በማም ረትና ፣ በማቅረብ በዘርፉ ለተሰማራው ተጠቃሚ እንዲዳረስ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ ፤

በግብርና ግብዓት ማምረት ፣ ማቅረብ ፣ ሥርጭትና ንግድ ተግባር ላይ እንዲሳተፉ የግል ባለሀብቶች ፣ መንግሥታዊ ድርጅ ቶችና ሌሎችም አግባብ ያላቸውን በማበረታታት የዘርፉን የሥራ ሂደት ማጠናከር በማስፈለጉ ፤

የግብርናውን ምርትና ምርታማነት በማሳደግ ቀጣይነት ያለው ልማት በሀገሪቱ ለማረጋገጥ የግብርና ግብዓቶችን በሥርዓት አስተባብሮና አቀናጅቶ መምራት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፤

በአጠቃላይ የአገሪቱን ወቅታዊና ዘላቂ የግብርና ልማት ፍላጐት ለማሟላት የሚያግዙ የግብርና ግብዓቶች አግባብ ባላቸው ሕጎችና ደንቦች መሠረት ጥራታቸው ተጠብቆ በወቅቱ እንዲቀርቡ በመከታተልና ቴክኖሎጂዎችንም ለማስፋፋት የሚያስችል አቅምና ክህሎት የመገንባት ፍላጎት በመኖሩና ይህንንም ሥራ የሚያስተባብርና የሚከታተል አካል ማቋቋም በማስፈለጉ ፤

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55(1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ።

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መለያ: አዋጅ ቁጥር 288/1994
ቀን: ሰኔ 30፥ 1994 ዓ.ም.
Law Type: Proclamations

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች

አዋጅ ቁጥር 1288/2015

•

ሐምሌ 17፥ 2015 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
አዋጅ ቁጥር 1289/2015

•

ሰኔ 29፥ 2015 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
ደንብ ቁጥር 527/2015

•

ታኅሣሥ 4፥ 2015 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
ደንብ ቁጥር 509/2014

•

ሚያዝያ 15፥ 2014 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
ደንብ ቁጥር 465/2012

•

መጋቢት 18፥ 2012 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ