ለመጠጥ ውሀ ልማትና መልሶ ማቋቋም ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የሚውል መጠኑ ኤስ.ዲ.አር 24 ሚሊዮን (ሃያ አራት ሚሊዮን ኤስ.ዲ.አር) የሆነ ገንዘብ የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በዓለም አቀፍ የልማት ማኅበር መካከል እ.ኤ.አ ሜይ 25 ቀን 1996 በዋሽንግተን ዲሲ የተፈረመ በመሆኑ፤
ይህንኑ የብድር ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥቅምት 14 ቀን 1988 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ያጸደቀው ስለሆነ፤
በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 55 (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል።
•
•
•
•
•
•
•
•
•