የሕብረተሰቡ ጤና ደህንነቱ፣ ፈዋሽነቱና ጥራቱ ካልተረጋገጠ ዘመናዊም ሆነ ባህላዊ መድኃኒት መጠበቅ ያለበት በመሆኑ፤
ደህንነቱና ጥራቱ ባልተጠበቀ ምግብ ምክንያት በሕብረተሰቡ ጤና ላይ ሊደርስ የሚችለውን የጤና ችግር መከላከል አስፈላጊ በመሆኑ፤
ደረጃውን ባልጠበቀ የጤና አገልግሎት እንዲሁም ብቃትና ሙያዊ ሥነ-ምግባር በጎደለው የጤና ባለሙያ፣ በአካባቢ ጤና አጠባበቅ ጉድለትና በተላላፊ በሽታዎች ቁጥጥር ጉድለት ምክንያት ሊደርስ የሚችለውን የጤና ችግር መግታት አስፈላጊ በመሆኑ፤
የናርኮቲክና ሣይኮትሮፒክ መድኃኒቶችንና እነዚህኑ ለማምረት የሚያገልግሉ ፕሪከርሰር ኬሚካሎችን ሕገወጥ ምርት፣ ሥርጭትና አጠቃቀም መከላከልና መግታት በማስፈለጉ፤
በጤናው ዘርፍ ሰፍኖ የቆየውን የተበታተነና ጥራት የጎደለውን የአስተዳደርና የቁጥጥር ስርዓት ቀልጣፋና ውጤታማ ለማድረግ አዲስና የተቀናጀ የምግብ፣ የመድኃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ሥርዓት ማስፈን አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ- መንግሥት አንቀጽ 55(1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•
•
•
•
•
•
•