የመሬት ባለቤትነት መብት የመንግሥትና የሕዝብ ብቻ መሆኑ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት በመረጋገጡ፤
በተለያዩ የሀገሪቱ የሥነ ምህዳር ቀጠናዎች ላይ ተመስርቶ ዘላቂ የገጠር መሬት አጠቃቀም ዕቅድ በማውጣትና በመተግበር የተፈጥሮ ሀብቶችን በዘላቂነት በመጠበቅና በማልማት ለመጪው ትውልድ ማስተላለፍ በማስፈለጉ፤
በሀገሪቱ የሚገኙ የተለያዩ የገጠር መሬት ዓይነቶችን ማለትም ይዞታ በወል፣ በግለሰብ ገበሬ እና በፌዴራልና በክልል መንግሥታት ሥር የሚገኙ ይዞታዎችን በስፋት፣ በአቅጣጫና በመሬት የመጠቀም መብቶች ለመለየት የሚያስችል መዘጋት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
የመረጃ ሥርዓት የግለሰብ ገበሬዎችን፣ የአርብቶ አደሮችንና የእርሻ ኢንቨስተሮችን ከማበረታታት አኳያ የሚታዩ ችግሮችን በመቅረፍ ምቹ የሆነ የገጠር መሬት አስተዳደር ሥርዓት መፍጠር አስፈላጊ በመሆኑ፤
ጥምር የሰብልና የእንስሳት ምርት እንቅስቃሴ በሠፈነባቸው አካባቢዎች የአፈር መሸርሸርና የደን መመናመን አደጋ በመኖሩ አርሶ አደሩ አስፈላጊውን እንክብካቤ እንዲያደርግ በይዞታው የመጠቀም መብቱ እንዲጎለብትና እንዲጠናከር ምቹ የሕግ ሁኔታዎች መፍጠሩ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በአርብቶ አደሮች አካባቢ በአብዛኛው በጎሣ ላይ በተመሠረተው የወል የመሬት ይዞታ ስሪት ውስጥ ለተፈጥሮ ሀብት አያያዝና አጠቃቀም እንዲሁም የግል ባለሀብቶችን ከማበረታታት አኳያ ተስማሚ የገጠርnመሬት አስተዳደር ሥርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ፤
መሬትንና የተፈጥሮ ሀብትን ለማስተዳደር ለክልሎች የተሰጠው ሥልጣን በሥራ ላይ የሚውለው የፌዴራል መንግሥቱ በሚያወጣው ህግ መሠረት መሆኑን የሕገ- መንግሥት አንቀጽ 52 (2) (መ) ስለሚደነግግ፣
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55 (1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•
•
•
•
•
•
•