የተሻረ

የኢትዮጵያ የአፈር ሀብት ኢንስቲትዩት ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ

ፈጣንና ዘለቂነት ያለው የግብርና ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ በቤተሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ በአየር ንብረት ለውጥ የሚከሰተውን አሉታዊ ተጽዕኖ ለመከላከልና ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት ጉልህ አስተዋፅዖ ለማድረግ ጤንነቱና ለምነቱ የተጠበቀ አፈር በማስፈለጉ፤

የአፈር ለምነትንና ጤንነት በዘላቂነት ለመጠበቅ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የመረጃ ሥርዓት መዘርጋት እንዲሁም ወቅታዊና ዝርዝር የአፈር ሀብት ለምነትና የመሬት ገጽታ መረጃ በማስፈለጉ፤

በተለያዩ የግልና የመንግስት ተቋማት የአፈር መረጃዎች የሚመነጩበት መንገድ ወጥ እና የጥራት ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን ማድረግ በማስፈለጉ፤ ዲጂታል የአፈር ሀብት ለምነትና የመሬት ገጽታ መረጃ ምንጨታ፣ ትንተናና ካርታ ዝግጅት ስራዎችን በሚፈለገው ጥራትና ፍጥነት ለማከናወን ጠንካራ አገራዊ አቅም መገንባት በማስፈለጉ፤

ዘመናዊ የጂኦስፓሻል ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም በማሳ ደረጃ የአፈር ለምነት ምርመራ ውጤትን፣ የእጽዋት የንጥረ ነገር ፍላጎትን እና ሥነ ምህዳርን መሰረት ያደረገ የአፈር ለምነት ማሻሻያ ቴክኖሎጂዎች አጠቃቀምና የአፈር አያያዝ ምክረ ሐሳቦችን ለአርሶ/አርብቶ አደሮች ለፖሊሲ አውጪዎችና ለሌሎች ተጠቃሚዎች በሚፈለገው አግባብ ተደራሽ ማድረግ በማስፈለጉ፤

ዘመናዊ የጂኦስፓሻል ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም በማሳ ደረጃ የአፈር ለምነት ምርመራ ውጤትን፣ የእጽዋት የንጥረ ነገር ፍላጎትን እና ሥነ ምህዳርን መሰረት ያደረገ የአፈር ለምነት ማሻሻያ ቴክኖሎጂዎች አጠቃቀምና የአፈር አያያዝ ምክረ ሐሳቦችን ለአርሶ/አርብቶ አደሮች ለፖሊሲ አውጪዎችና ለሌሎች ተጠቃሚዎች በሚፈለገው አግባብ ተደራሽ ማድረግ በማስፈለጉ፤

ከአፈር ጋር ተያያዥነት ያላቸውን የግብርናና ገጠር ልማት ፖሊሲና ስትራቴጂውን፣ የአሰራር ስርዓቶችንና ተያያዥ የህግ ማዕቀፎችን ውጤታማ አፈጻጸም ለማረጋገጥ ጠንካራ ተቋም በማስፈለጉ፣

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 916/2008/2008 (በአዋጅ ቁጥር 942/2008 እንደተሻሻለ) አንቀጽ 5 እና 38መሰረት ይህንን ደንብ አውጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መለያ: ደንብ ቁጥር 418/2010
ቀን: ሕዳር 15፥ 2010 ዓ.ም.
Law Type: Regulations

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች

አዋጅ ቁጥር 1288/2015

ሐምሌ 17፥ 2015 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
አዋጅ ቁጥር 1289/2015

ሰኔ 29፥ 2015 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
ደንብ ቁጥር 527/2015

ታኅሣሥ 4፥ 2015 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
ደንብ ቁጥር 509/2014

ሚያዝያ 15፥ 2014 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
ደንብ ቁጥር 465/2012

መጋቢት 18፥ 2012 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ