በአገልግሎት ላይ

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት እና ፈንድ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1354/2017

ጥራታቸው የተረጋጋጠ መሠረታዊ መድኃኒቶችን በተመጣጣኝ ዋጋና ዘላቂነት ባለው መልኩ ለተጠቃሚው ሕብረተሰብ ማቅረብ የሚያስችል የማይበገር ዘመናዊ የመድኃኒት አቅርቦት ሠንሰለት ሥርዓት መዘርጋት  አስፈላጊ በመሆኑ፤

የአገልግሎቱን የፈንድ ምንጭ በማስፋት በመንግሥት የጤና ተቋማት አስተማማኝ እና የማያቋርጥ የመድኃኒት አቅርቦት እንዲኖር ማድረግና የህብረተሰብ ፍትሐዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ አስራርመቀየስ ተገቢ በመሆኑ፤

የመሠረታዊ መድኃኒቶች አቅርቦትን በማሻሻ፤ የመድኃኒት ፈንድ ምንጭን፣ የመሠረታዊ መድኃኒቶች መጠባበቂያ ክምችት አስተዳደርን እንዲሁም ተያያዥ አሰራሮችን ለማጠናከር የሚያስችል በቂ የሕግ መሠረት በማስፈለጉ፣

መድኃኒት ለጤና አገልግሎት ወሳኝ ድርሻ ያለው በመሆኑ እና ለጤናው ዘርፍ ከሚመደበው መዋዕለ ነዋይ ዉስጥ የመድኃኒት ግዥ ከፍተኛውን ድርሻ ስለሚይዝ ይህን ከፍተኛ ገንዘብ በአግባቡና ለታለመለት ዓላማ መዋል የሚያስችል ዉጤታማ እና የአገር ዉስጥ የመድኃኒት አምራቾችን የሚያበራታታ የመድኃኒት አቅርቦት ሥርዓት መዘርጋት ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ በመሆኑ፣

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55(1) መሠረት የሚከተለው ታዉጇል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መለያ: አዋጅ ቁጥር 1354/2017
ቀን: መጋቢት 4፥2017 ዓ.ም.
Law Type: Proclamations

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች

1434/2018

ሐምሌ 23÷ 2018 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
1425/2018

ሐምሌ 16÷ 2018 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
1426/2018

ሐምሌ 14÷ 2018 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
592/2018

ሐምሌ 3÷ 2018 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ