በተፈጥሮ ለሚመረቱ የግብርና ምርቶችና ከእነዚሁ ለሚገኙ የምግብ ሸቀጦች በሸማቾች በኩል ያለው ፍላጐት በዓለም አቀፍ ደረጃ እያደገ በመምጣቱ በሀገራችን በተፈጥሮ ግብርና ሊመረቱ ለሚችሉ ምርቶች አዲስ ገበያ የሚፈጥር በመሆኑ፤
እንደእነዚህ ላሉት ምርቶች ያለው የገበያ ዋጋም ከፍተኛና ለገጠሩ ኅብረተሰብ የተሻለ ዋጋና የኢኮኖሚ ዕድገት ለማስገኘት ጠቀሜታ ያለውና የአመራረት ዘዴውም የመሬትን ለምነት፣ ብዝሃ ሕይወትንና የአካባቢ ደህንነትን ለመጠበቅ አስተዋፅኦ ሊያደርግ የሚችል በመሆኑ፤
እያደገ የመጣውን የምርቱን ተፈላጊነት ለማርካትም የግብርና ምርቶችና የምግብ ሸቀጦች በተፈጥሮ ወይንም ሰው ሰራሽ የሆነ ኬሚካል ጥቅም ላይ ሳይውል የተመረቱ መሆናቸውን የሚገልጹ ወይንም ይህ ዓይነቱ እንድምታ ያላቸው ምልክቶች እየተደረጉባቸው ለሸማቾች በገበያ ውስጥ በመቅረብ ላይ የሚገኙ መሆናቸውን ማሳየቱ አስፈላጊ በመሆኑ፤
በሀገራችን በመካሄድ ላይ የሚገኘው የግብርና ምርቶች የአመራረት ሥርዓት የተፈጥሮ ግብርና አመራረት ዘዴ የሚጠይቀውን መስፈርት የሚያሟላና በቀላሉ ምርቱን ለዓለም ገበያ ማቅረብ የሚያስችል በመሆኑ፤
ለተፈጥሮ የግብርና ምርቶች ገበያ ያላቸው አገሮችም እንደእነዚህ ያሉትን ምርቶች ለመጠቀም የሚያስችሉ ደንቦችን ያፀደቁና የኢንስፔክሽን ሥርዓቶችንም የዘረጉ በመሆናቸው፤
የተፈጥሮ የአመራረት ዘዴዎችን በመጠቀም የተመረቱ መሆናቸውን የሚገልጹ ምልክቶች የሚደረጉባቸው የግብርና ምርቶችን በሚመለከት የአምራቾችንና የሸማቾችን ጥቅም ለማስጠበቅ መሟላት የሚገባቸውን መሠረታዊ መስፈርቶች በሀገራችንም በግልጽ ማስቀመጥ የሚገባ በመሆኑ፤
ይህም የአመራረት፣ የአደረጃጀትና የአሰረጫጨትሥርዓት በሌሎች አገሮች የተለመደና ተቀባይነት ያገኘ በመሆኑ በአገራችን እንዲሰራበት በተፈጥሮ ዘዴ የተመረቱ መሆናቸውን የሚጠቅሱ ምልክቶችን የሚጠቀሙ ኦፕሬተሮች የተወሰኑትን መሠረታዊ መስፈርቶች ማሟላታቸውን ለማረጋገጥ ዕውቅና ባላቸው የኢንስፔክሽንና የሰርተፊኬሽን አካላት በመደበኛነት በሚከናወኑ የክትትል ሥርዓቶች ውስጥ ማለፍየሚገባቸው በመሆኑ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55 (1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•
•
•
•
•
•
•
•
•