የአፍሪካ ሕብረት በምግብ እጥረትና ድርቅ ምክንያት በየጊዜው በአህጉሪቱ የሚከሰተውን ረሀብ ለማስወገድ የግብርና ምርትን በሙያ፣ በማዳበሪያ አቅርቦትና በሌሎች የቴክኒክ እርዳታዎች በመታገዝ ማሳደግ አስፈላጊ መሆኑን በመገንዘብ እ.ኤ.አ. ጁን 2 ቀን 2006 የአፍሪካ የማዳበሪያ ልማት ማዕከል በሐራሬ ዚምባብዌ እንዲቋቋም በመወሰኑ፤
አገራችን ይህን ኮንቬንሽን እ.ኤ.አ. ዲሴምበር 28 ቀን 2007 የፈረመች በመሆኑ፤
ይህንኑ ቻርተር የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥቅምት 27 ቀን 2001 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ያጸደቀው በመሆኑ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ- መንግሥት አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀፅ (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•
•
•
•
•