ለሳውላ ቀይ አፈር የገጠር ኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል መጠኑ 20 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር (ሃያ ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር) የሆነ ገንዘብ የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በኦፔክ ፈንድ ለዓለም ዓቀፍ ልማት መካከል እ.ኤ.አ. ኖቬምበር 19 ቀን 2007 በቪየና የተፈረመ በመሆኑ፣
ይህንኑ የብድር ስምምነት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት ሚያዝያ 30 ቀን 2000 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ያጸደቀው ስለሆነ፤
በሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55 (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል።