የማይፈለጉ አካባቢያዊና ማሕበራዊ ተፅዕኖዎችን ለማስቀረት የሚያስችሉ የግብርና አሠራሮችን በአበባ ልማት ዘርፍ መተግበር አስፈላጊ በመሆኑ፤
አካባቢያዊ አዛላቂነት እና ማሕበራዊ ተቀባይነት ያለው የግብርና አሠራርን ምንነት መግለፅ እና መደንገግ የአበባ ኢንዱስትሪን አዛላቂነት ስለሚያጎለብት፤
የኢትዮጵያ የአበባ ኢንዱስትሪን መልካም ዝና ከፍ ለማድረግ እንዲቻል የማሕበራዊ እና የአካባቢ የኃላፊነት ደረጃዎችን የሚወስን የምስክር ወረቀት አሰጣጥ ሥርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ፤
የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር የ 691/2003 አንቀፅ 5 እና በአካባቢ ብክለት ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 300/1995 አንቀጽ 20 መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል፡፡
•
•
•
•
•
•
•
•
•