በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥትና በጣሊያን ሪፐብሊክ መንግሥት መካከል በጉምሩክ ሕጎች ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን በጋራ ለመከላከል፣ ለመመርመርና ለመግታት የሚያስችል የትብብር ስምምነት መስከረም 16 ቀን 1999 ዓ.ም በሮም ጣሊያን ላይ የተፈረመ ስለሆነ፤
ስምምነቱ መረጃዎችን ለመለዋወጥ የቴክኒክ ሥልጠናዎችን ለማስገኘት እና የኢትዮጵያ ጉምሩክ ባለሥልጣንን አቅም ለመገንባት እና ችግሩን ለመቅረፍ የሚያግዝ በመሆኑ፤
ይህንኑ ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሚያዝያ 16 ቀን 1999 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ያፀደቀው ስለሆነ፤
በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ (1) እና (1) መሠረት ከዚህ የሚከተለው ታውጇል፡፡
•
•
•
•
•
•
•
•
•