በአገልግሎት ላይ

ስለራስ-ገዝ ዩኒቨርሲቲ ለመደንገግ የወጣ አዋጅ

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ነፃ ሆነው እንዲሰሩ ማድረግና በሁሉም ሥራዎቻቸው ላይ በራሳቸው እንዲወስኑ ለተቋማቱ ማድረግ ውጤታማነትና ብቃት መሻሻል፣ ለአገር እድገት፣ ብቃት ያለው የሰለጠነ የሰው ሀብት ለማፍራት፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪነትን ለመገንባት ያላቸውን ትልቅ አስተዋፅኦ በመረዳት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ፣ ጥልቅ በሆነ የመማር-ማስተማር እና የምርምር ሥራ የዳበረ ዕውቀት የሚገኝባቸው የፈጠራ ሀሳብና ሥራ የሚስፋፋባቸው፣ በማኅበረሰብ ጉድኝት ለሕብረተሰቡ ተገቢውን የጤናና ሌሎች አገልግሎቶች ጥራቱን ጠብቆ በሰፊው የሚሰጥባቸው ይሆኑ ዘንድ፣ ለሰው ልጆች ዕድገትና ልማት የተሰለፉና ሥራቸውንም በሙሉ ነፃነት የሚያከናውኑ ተመራማሪዎችን መምህራንን፣ ሠራተኞችንና ተማሪዎችን ያቀፉ ተቋማት አድርጎ እንደገና ማደራጀት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የራሳቸውን የገቢ ምንጮች በማስፋፋት፣ ገቢያቸውን እንዲያሳድጉ በማድረግ ሀገራዊ የልማት ትልሞችን ለማሳካት እንደሚያስችል በመታመኑ፤

ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከላይ የተዘረዘሩትን ዓላማዎች ለማሳካት እንዲያስችላቸው ለተሻለ የአካዳሚያዊ የፋይናንስና የአስተዳደር ነፃነቶች የራስ-ገዝ እንዲሆኑ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ እና አዲስ ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ሊቋቋም የሚችልበትን ሥርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ፤

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ- መንግሥት አንቀፅ 55(1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መለያ: አዋጅ ቁጥር 1294/2015
ቀን: መስከረም 25፥ 2016 ዓ.ም.
Law Type: Proclamations

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች

ደንብ ቁጥር 561/2016

•

ህዳር 23፥ 2017 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
አዋጅ ቁጥር 351/1995

•

ሰኔ 26፥ 1995 ዓ.ም.
የተሻረ