ኢትዮጵያ ያላት ከፍተኛ ብዝሀ ህይወት ፀጋ ለሕዝቦቿ ጥቅምና ብልጽግና እንዲውል በአግባቡ መጠበቅና በዘላቂነት ጥቅም ላይ መዋል ያለበት በመሆኑ፤
ብዝሀ ህይወትን በመንከባከብ፣ በማበልፀግና በዘለቂነት በመጠበቅ ረገድ የኢትየጵያ ማህበረሰቦች ላደረጉት ታሪካዊ አስተዋጽኦ እውቅና መስጠትና ይህንን አስተዋጽኦቸውን እንዲቀጥሉበት ማበረታታት አስፈላጊ በመሆኑ፤
የኢትዮጵያ የብዝሀ ህይወት ኮንቬንሽንን የተቀበለች እና የኮንቬንሽኑንም አርክቦት ህግ እንዲወጣ የሚጠይቅ በመሆኑ፤
የማህበረሰቦች፣ የአርሶ አደሮችንና የዕፅዋት መብት እንዲሁም የሕይታዊ ሀብት አዳቃዮችን አርክቦትን በሚመለከት የወጣውን የአፍሪካ ሕግን ኢትዮጵያ የተቀበለች በመሆኑ፤
የጀነቲክ ሀብት እንዲጠበቅና በዘላቂነት ጥቅም ላይ እንዲውል ለማድረግ የሚያስችልና የኢትዮጵያ ማሀበረሰቦች ያዳበሩት ልማዳዊ የጀነቲክ ሀብት ክብካቤና አጠቃቀም ሥርዓት ሊጠበቅና ሊበረታታ የሚገባው በመሆኑ፤
የጀነቲክ ሀብት ክብካቤና አጠቃቀምን በሚመለከት የኢትዮጵያ ማህበረሰቦች ያካበቱትና ያዳበሩት ዕውቀት እውቅና ሊያገኝና ጥበቃ ሊደረግለት እንዲሁም በእነዚህ ማህበረሰቦች ፈቃድና የጥቅም ተከፋይነት በሰፊው ጥቅም ላይ እንዲውል ሊበረታታ የሚገባው በመሆኑ፤
የጀነቲክ ሀብት ጥቅም ላይ እንዲውል በመፍቀዱና ጥቅም ላይ መዋሉ ከሚገኘው ገቢ በመጋራት ረገድ በሚሰጥ ውሳኔ ላይ የአካባቢ ማህበረሰቦች እንዲሳተፉ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ፤
እነዚህን ዓላማዎች በተግባር ለማዋል የጀነቲክ ሀብትና የማህበረሰብ ዕውቀት አርክቦትና ማህበረሰቦች በጀነቲክ ሀብታቸውና የማህበረሰብ ዕውቀታቸው ላይ ያላቸውን መብት በሕግ መወሰን አስፈላጊ በመሆኑ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55 (1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•
•
•
•
•
•
•
•