በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በስዊዘርላንድ መንግስታት መካከል የሰብዓዊ እርዳታ፤ የቴክኒክ እና የፋይናንስ ትብብር ስምምነት እ.ኤ.አ ጁላይ 15, 2015 በአዲስ አበባ የተፈረመ ስለሆነ፤
ስምምነቱ ሥራ ላይ የሚውለው በተዋዋዮቹ አገሮች ሕግ መሰረት መፅደቁን የሚያረጋግጡ ሰነዶች ልውውጥ ከተደረገበት ቀን ጀምሮ በመሆኑ፣
ይህንኑ ስምምነት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሚያዚያ 6 ቀን 2008 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ያፀደቀው ስለሆነ፤
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግስት አንቀፅ 55 (1) እና (12) መሰረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•
•
•
•
•
•
•
•