በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገመንግሥት ሀሳብን በነፃ የመግለፅና የመገናኛ ብዙሃን ነፃነት የተረጋገጠ በመሆኑ፣
መገናኛ ብዙሃን በነፃነት ለመንቀሳቀስ ይችሉ ዘንድ የቅድሚያ ምርመራ ገደብ እንዳይጣልባቸው ሕገ-መንግሥቱ ዋስትና የሰጠ መሆኑን በአጽንኦት በመገንዘብ፤
የወጣቶችን ደህንነት፣ የሰውን ክብርና መልካም ስም፣ ብሔራዊ ደህንነትን፣ የህዝብ ሰላምና ፀጥታን እንዲሁም ሌሎች ተነጻጻሪ መብቶችና ጥቅሞችን ለማስጠበቅ ሲባል በግልጽ በሚደነገጉ ሕጎች ብቻ ሃሳብን በነፃ በመግለፅና በመገናኛ ብዙሃን ነፃነት ላይ ገደቦች እንዲጣሉ የሚያዘውን ህገ መንግስታዊ መርህ በማረጋገጥ፣
በዜጎች መሀከል በሚደረገው ነፃ የሀሳብና የመረጃ ልውውጥ እንዲሁም በመገናኛ ብዙሃን የአሰራር ነፃነት ላይ መሰናክል የነበሩ ተቋማዊ እና መዋቅራዊ ችግሮችን በማስወገድ በነፃ ሀሳብን የመግለፅና የመገናኛ ብዙሃን ነፃነትን አስመልክቶ ያዳበርናቸውን አዎንታዊ እና ገንቢ ልምዶች የመጠበቅና ይበልጥ የማጠናከርን አስፈላጊነት በመረዳት፣
በሀገራችን ዴሞክራሲያዊ ስርአትን ለመገንባት የሚደረገው ጥረት ስኬታማ የሚሆነው መተኪያ የሌለው ታላቅ ሚና መጫወት የሚችል ራሱን በከፍተኛ ስነምግባር በማነፅ በከፍተኛ ሙያዊ ብቃት የሚንቀሳቀስ ነፃና ፈርጀ ብዙ የመገናኛ ብዙሃን ሲኖር ብቻ መሆኑን በመገንዘብ፣
መገናኛ ብዙሀን በህገመንግስቱ ለተረጋገጡ መሰረታዊ ነፃነቶችና መብቶች መከበር እንዲሁም ለሰላም፣ ለእኩልነት፣ ለፍትህና ለዴሞክራሲ የቆሙ መሆኑን በመረዳት፣
መገናኛ ብዙሃን አጋላጭ የሆኑትን ጨምሮ መረጃዎች የመሰብሰብና የማሰራጨት መብት ያላቸው መሆኑን በመገንዘብ፣ በህዝቦች መካከል ነጻ የሃሳብና የመረጃ ልውውጥ የሚያመቻችና ዜጎች በነጻ መረጃና አስተያየትን ለመሰብሰብ፣ ለመቀበልና ለማስተላለፍ ያላቸውን መብት ሙሉ በሙሉ እንዲያረጋግጡ የሚያስችላቸው ጤናማ የመረጃ ስርዓት ያልተገደበ ዲሞክራሲያዊ የህዝብ ውይይት መድረክ በመሆን ለሚያገለግል ነጻ የመገናኛ ብዙሃን ህልውና እጅግ አስፈላጊ መሆኑን በመገንዘብ፣
የመንግስት ግልፅ አሰራር፣ በተለይም የማንኛውም ግለሰብ በመንግስት አካላት እጅ የሚገኙ መረጃዎችን የማግኘት መብት ለዴሞክራስያዊ ህብረተሰብ ያለውን መሰረታዊ ጠቀሜታ በመረዳት፣
በህገመንግስቱ የተረጋገጡትን ግልፅ የመንግስታዊ አሰራርና የተጠያቂነትን እሴቶች ለማዳበርና ይበልጥ ለማጠናከር እንዲሁም የህዝብ ጥቅምን የሚመለከቱ ጉዳዮች ይፋ ወጥተው ህዝብ እንዲወያይባቸው ለማድረግ ይቻል ዘንድ፤ የመንግስት ኃላፊዎች ለግለሰቦችና ለመገናኛ ብዙሃን መረጃዎችን የማቅረብ ግዴታ በህግ እንዲጣልባቸው ለማድረግ፣
በስራ ላይ ያለውን የፕሬስ አዋጅ በማሻሻል በኢትዮጵያ በመካሄድ ላይ ከሚገኘው ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ጋር በሚጣጣም አዲስ ህግ መተካቱ አስፈላጊ መሆኑን በመረዳት፣
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ሕገመንግሥት አንቀጽ 5() መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•
•
•
•
•
•
•
•