የኢንፎርሜሽንና የኮምኒዩኬሽን ቴክኖሎጂ ለሃገሪቱ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ እድገት ቁልፍ ሚና የሚጫወት በመሆኑ፤
የኢንፎርሜሽንና የኮምኒዩኬሽን ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ተገቢ ጥንቃቄና ጥበቃ ካልተደረገለት የሃገሪቱን ሁለንተናዊ እድገት ሊያደናቅፍ እንዲሁም የዜጎችን የግል ነፃነት አደጋ ላይ ሊጥሉ ለሚችሉ የተለያዩ የኮምፒዩተር ወንጀሎች እና ሌሎች የደህንነት ስጋቶች የተጋለጠ በመሆኑ፤
በሥራ ላይ ያሉ የሀገሪቱ ሕጎች ከአዳዲስ የቴክኖሎጂ ለውጦች ጋር በበቂ ሁኔታ ተጣጥመው የማይሄዱ እና የኮምፒዩተር ወንጀልን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠር፣ ለመመርመርና ተጠርጣሪዎችን ወደ ፍትህ ለማቅረብ የሚያስችሉ ባለመሆናቸው፤
የኮምፒዩተር ወንጀልን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠር፣ ለመመርመርና ኤሌክትሮኒክ ማስረጃዎችን ለመሰብሰብ የሚያስችሉ አዳዲስ ስልቶችንና ሥርዓቶችን በሕግ መደንገግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ህገ መንግስት አንቀጽ 55 (1) መሰረት የሚከተለው ታውጇል፡-
•
•
•
•
•
•
•