የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ለተፋጠነ ሀገራዊ የፖለቲካ የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት የሚኖረውን ከፍተኛ ድርሻ ፈር በያዘና ውጤታማ በሆነ አቅጣጫ በመምራት መጠቀም አስፈላጊ በመሆኑ፤
የኢንፎርሜሽንና ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂን የዕድገት ፍጥነት፣ ባህሪና ሽፋንን ያገናዘበና በመስኩ የጥምረት ገጽታ ላይ የተመሠረተ ሀገራዊ ዕድገት እንዲኖር ማድረግ በማስፈለጉ፤
የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ እንደ አንድ የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ልማት ዘርፍ ጎልብቶ በአገርና በዓለም አቀፍ እንቅስቃሴ ተወዳዳሪ የጥራት ደረጃ እንዲኖረው የተቀናጀ እርምጃ በመውሰድ ዕድገቱ እንዲረጋገጥ ማድረግ በማስፈለጉ፤
ከላይ የተገለጹትን ዓላማዎች ለማሳካትና በአገር አቀፍ ደረጃ የኢንፎርሜሽንና ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ልማትን ለማፋጠን በኃላፊነት የሚያስፈጽም መንግሥታዊ አካልን ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55(1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል።
•
•
•
•
•
•