የመመሪያ መለያ: 76/2014
ቀን: ሰኔ 21፥ 2011 ዓ.ም.
Language: Amharic

የቅሬታና አቤቱታ አቀራረብና አፈታት ሥርዓት (መመሪያ ቁጥር 76/2014)

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የሰው ሀብት አስተዳደር ስርዓቱን ውጤታማ ለማድረግ፣ በየጊዜው ወቅቱን የሚመጥን የማሻሻያ ስራ ለማከናወን፣ ብልሹ አሠራርን ለማስወገድ፣ የሰራተኞችን ተነሳሽነት ለማሳደግ፣ ሰራተኞችን ለመሳብና ለማቆየት እና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ዋነኛው የሪፎርም አካል መሆኑን ግምት ውስጥ በማስገባት ትኩረት ሰጥቶ በመሥራት ላይ ይገኛል፤

በዚህም መሠረት የሰው ሀብት ስምሪት አይነት ከሆኑት መካከል የዝውውር አሠራር አንዱ በመሆኑ የግልጸኝነትና ተጠያቂነት አሠራርን ለማስፈን በሚደረገው እንቅስቃሴ ትኩረት የተሰጠው የስምሪት አይነት በመሆኑ ከሌሎች መመሪያዎች ጋር በየደረጃው የሚገኙ የሰው ሀብት ስራ አመራር ባለሙያዎችና የሚመለከታቸው ከአስተዳደሩ ውጪ የሆኑ ባለድርሻ አካላት ጭምር ውይይትና ተሳትፎ ካደረጉበት በኋላ የተለያዩ ግብዓቶችን በማሰባሰብ ከ2002 ዓ.ም ጀምሮ በስራ ላይ የቆየውን የዝውውር አፈፃፀም መመሪያ በማሻሻል በመንግሥት ሠራተኛ አዋጅ 56/2010 በአንቀጽ 97 ንዑስ አንቀጽ 2 መሠረት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ይህንን የመንግሥት ሠራተኞች የተሻሻለውን የዝውውር አፈፃፀም መመሪያ አውጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ

Addis Ababa City Administration Industry Development Bureau

Similar Directives

ኅዳር 1፥ 2017
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን
Addis Ababa City Administration Fire and Disaster Risk Management Commission
ጥር 5፥ 2017
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን
Ethiopian Agricultural Authority
ህምሌ 29፥ 2016
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ
National Bank Of Ethiopia
መጋቢት 20፥ 2016
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን
Ethiopian Capital Markets Authority
ታኅሣሥ 19፥ 2016
የኢትዮጵያ ህብረት ስራ ኮሚሽን
Ethiopian Cooperative Commission