የጤናው ዘርፍ የልማት እቅዶችን ለማስፈጸም ከለጋሽ ድርጅቶች የሚገኝ ገንዘብ አስተዳደር እና አጠቃቀም ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ማስተካከል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
ጠንካራ የቻናል-2 ፋይናንስ የአስተዳደር እና የውስጥ ቁጥጥር ስርዓትን በመዘርጋት በጀቱ በአግባቡ እና ለታለመለት ዓላማ እንዲውል እና ለክልል ጤና ቢሮዎችና አስፈፃሚዎች የሚተላለፈው ገንዘብን በወቅቱ ማወራረድ በማስቻል ወጭ ቆጣቢ እና ውጤታማ የሆነ የፋይናንስ አጠቃቀም ስርዓትን በማጎልበት ተጨማሪ ሀብት ማስገኘት እንዲቻል ለማድረግ፣
የቻናል-2 ፋይናንስን የሚጠቀሙ የተለያዩ ተቋማት ጥራቱን የጠበቀ እና ወቅታዊ የአፈጻጸም ሪፖርት የሚያቀርቡበትን የአሠራር ስርዓት በመዘርጋት ግልጽነት እና ተጠያቂነትን በማስፈን በፕሮግራም እና በፋይናንስ አስተዳደር መካከል የተናበበ እና የተቀናጀ አሠራር በመዘርጋት ለወጣው ወጭ ተመጣጣኝ ውጤት ማስገኘት የሚያስችል የአሠራር ስርዓት መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
የገንዘብ ሚኒስቴር በፌዴራል መንግሥት የፋይናንስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 648/ 2001 አንቀጽ 75 መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል።