የመመሪያ መለያ: 978/2016
ቀን: ታኅሣሥ 19፥ 2016 ዓ.ም.
Language: Amharic

የኅብረት ሥራ ማህበራት ኦዲት አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 978/2016

የኅብረት ሥራ ማህበራት ኦዲት በማድረግ ሂደት አግባብ ያለው ባለሥልጣን፣ ኅብረት ሥራ ማህበራት እና የኅብረት ሥራ ኦዲተሮች ሊኖራቸው የሚገባ ተግባር እና ኃላፊነት ግልጽ ማድረግ በማስፈለጉ፣ የኅብረት ሥራ ማህበራት ጤናማነታቸውና ደህንነታቸውን እንዲረጋገጥ ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ ኦዲት በማድረግ ሽፋኑን ለማሳደግ የውክልና ኦዲት ተግባራዊ ለማድረግ የአሠራር ሥርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ፣

በኅብረት ሥራ ኦዲት ሪፖርት ላይ ለሚቀርቡ ቅሬታዎች ወጥ የሆነ የቅሬታ አፈታት ሥርዓት እንዲኖር በማስፈለጉ፣ የኅብረት ሥራ ማበኅራት ከምዝበራና ብልሹ አሠራር የፀዱና ጤናማ የሆነ ደህንነታቸው የተጠበቀ የፋይናንስ ስርዓት እንዲኖራቸው ቀጣይነት ያለው የኦዲት አገልግሎት በመስጠት ኦዲት ማድረግ በማስፈለጉ፤ የኀብረት ሥራ ኦዲተር ዓለም ዓቀፍ ተቀባይነት ያለውን የኦዲት ስታንዳርድ ተከትሎ እንዲሰራ፣ መብትና ግዴታዎችን እንዲሁም የስነምግባር መርሆዎችን አውቆ ስራውን እንዲያከናውን ማድረግ በማስፈለጉ፤

የኀብረት ሥራ ኦዲተር ሙያዊ ብቃትና ገለልተኛነቱ እንዲረጋገጥ እና እንደ አገር ወጥ የሆነ የኅብረት ሥራ ኦዲት አፈጻጸም ስርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ፣ የኀብረት ሥራ ኦዲተር የሚያዘጋጁት የኦዲት ሪፖርት በሁሉም የሪፖረቱ ውጤት ተጠቃሚዎች ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖረው ማድረግ በማስፈለጉ፣

በኅብረት ሥራ ማህበራት አዋጅ ቁጥር 985/2009 አንቀጽ 76(3) ፣ የኅብረት ሥራ ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 274/1996 አንቀጽ 5 እና የአስፈጻሚ አካላትን ሥልጣን እና ተግባር መወሰኛ አዋጅ ቁጥር 1263/2014 አንቀጽ 78(2) መሠረት በማድረግ የኢትዮጵያ ኀብረት ስራ ኮሚሽን ይህን መመሪያ አውጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የኢትዮጵያ ህብረት ስራ ኮሚሽን

Ethiopian Cooperative Commission

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration