የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች እና የሥራ ወጪውን ለመሸፈን ተመጣጣኝ የአገልግሎት ክፍያ እንዲወስንና ከካፒታል ገበያ ተሳታፊዎች እንዲሰበስብ በካፒታል ገበያ አዋጅ ሥልጣን የተሰጠው በመሆኑ፣
በባለሥልጣኑ የሚሰበሰበው ክፍያ ግልጽና ለሕዝብ ተደራሽ መሆን አስፈላጊ በመሆኑ፣
ባለሥልጣኑ በካፒታል ገበያ አዋጅ ቁጥር 1248/2013 አንቀጽ 108 (2) መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል።