ኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር ያዘጋጀውና ባሕላዊ የግጭት መፍቻ ዘዴዎች በፍትሕ አስተዳደር ሥርዓት ውስጥ ያላቸው ሚናና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩረው አህጉራዊ ኮንፍረንስ “Strengthening Traditional Dispute Resolution For Access To Justice In Africa” በሚል ርዕስ በመዲናችን አዲስ አበባ የአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም መጋቢት 16/2018 ዓ.ም መካሄድ ጀምሯል።
የኮንፍረንሱ ተሳታፊዎች በሚኖራቸው የሁለት ቀን ቆይታ በአህጉሪቱ በሚገኙ ባህላዊ የግጭት መፍቻ ዘዴዎች ላይ በጋራ ይወያያሉ፣ ዕርስ በርሳቸው ካላቸው ልምድ ይማማራሉ እንዲሁም ትብብሮችን ይፈጥራል ተብሎ ይታመናል፡፡
በኮንፍረንሱ ሃገራችን ኢትዮጵያን ጨምሮ ከተለያዩ አፍሪካ ሀገራት የተወጣጡ የፍትሕ እና ዳኝነት አካላት፤ሚኒስትሮች፤ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች፤አለማቀፍ የአጋር አካላት ተወካዮች ፤ሲቪል ማህበረሰባት ፤ የሃገር ሽማግሌዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳታፊ ናቸው፡፡