በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈፀም ጥቃትን ለመከላከል እና ምለሽ ለመስጠት የተቋቋመውን ብሔራዊ አስተባባሪ አካል ቅንጅታዊ አሰራርን ለማጠናከር ያለመ የውይይት መድረክ ተካሄደ

Forum Held to Strengthen Coordination of the National Body Tasked with Preventing and Responding to Violence Against Women and Children

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈፀም ጥቃትን ለመከላከል እና ምላሽ ለመስጠት የተቋቋመውን ብሔራዊ አስተባባሪ አካል ቅንጅታዊ አሰራርን ለማጠናከር ያለመና ከፌዴራል፣ ከከተማ መስተዳደር እና ከክልል ከተወጣጡ ባለድርሻ አካላት ጋር ግንቦት 15 ቀን 2018 ዓ.ም በቢሾፍቱ ከተማ ውይይት አካሂዷል፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ በሴቶችና ሕፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶችና ወንጀሎችን ለመከላከል ተፈፅሞ ሲገኝም ምላሽ ለመስጠትና ለማስቀጣት ተቋቁሞ ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ ሲሰራበት የነበረውን ስትራቴጂ በመገምገም ከቀድሞ ስትራቴጂ በተለየ መልኩ ለመከላከል ፣ ምላሽ ለመስጠት ፣መረጃ ለመያዝ ፣ስርዓትን ለመዘርጋትና ጠንካራ ቅንጅታዊ አሰራርን ለማጠናከር ብሎም የትኩረት አቅጣጫዎችን የያዘ ከ2016 -2020 ዓ.ም የሚቆይ ሁለተኛው ስትራቴጂ ተቀርፆ ወደስራ መግባቱ ተገልጿል፡፡

በተየያያዘ በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈፀም ጥቃትን ለመከላከል እና ምላሽ ለመስጠት የተቀረፀው ብሔራዊ ስትራቴጂ በአጠቃላይ በቀድሞው ስትራቴጂ ጥንካሬዎች ላይ ተመስርቶ የተቀረፀ መሆኑን፤ እንዲሁም በዋናነት ግን የቀድሞው ስትራቴጂ የነበረበትን ውስኑነቶች ለመቅረፍ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን የተገለፀ ሲሆን ፤ይህንንም በማድረግ ሂደት ውስጥ በሴቶችና ሕፃናት ላይ የሚፈፀም ጥቃትን ለመከላከል እና በፍትሕ ስርዓት ውስጥ የሚያልፉ ህፃናትን መብት ለማስጠበቅ በአዲስ መልክ ለመንቀሳቀስ ዘርፈ-ብዙ እና በርካታ ባለድርሻ አካላት ያስተባበር ስለመሆኑ ተወስቷል፡፡

በውይይት መድረኩ ያሉ ችግሮችን ታሳቢ በማድረግ ብሔራዊ አስተባባሪ አብይ ኮሚቴው ከፌዴራል፣ ከከተማ መስተዳደርና ከክልል ጉዳዮ በቀጥታ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በቅንጅት በክልል፤ በዞን እና በወረዳ ወጥ /ተመጋጋቢ/ እንዲሆን የሚያስችሉ ተግባራትን እና የአንድ ማዕከል አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል ተግባራዊ የሚደረግ የድርጊት መርሐ-ግብር ዙሪያ በመወያየት አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

Tagged Under: 16 days of activism against gender-based violence african charter on the rights and welfare of the child against and healthcare administration and control authority body child children convention on the elimination of all forms of discrimination against women (cedaw) Convention on the Rights of the Child convention on the rights of the child (crc) Coordination event Forum gains National res task un convention on the rights of the child violence Violence Against Children violence against women women Women and Children
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች