በጋምቤላ ክልል በ3ዓመቱ የፍትሕ ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን የ6ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ዙሪያ ክትትል ተደረገ

Monitoring was conducted on the 6-month performance of the 3-year Justice Sector Transformation Plan in the Gambella Region

በጋምቤላ ህዝቦች ክልል በፍትሕ ሚኒስቴር አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ በክቡር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ የተመራ የፍትህ ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን ግብረሃይል የክልሉን የሶስት አመት የፍትሕ ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት እቅድ አፈጻጸም የክልሉ ምክር ቤት ሀፈጉባዔ በተገኙበት ውይይትና ምልክታ አድርጓል፡፡

በክልሉ በፍትሕ ዘርፉ የታቀዱና በየዘርፉ የተጀመሩ ስራዎችን በተመለከተ በቀረበ ሪፓርት በፍትህ ዘርፉ የሚገኙ ባለሙያዎችን ሰነድና ብቃት የማጥራት ስራዎች ጨምሮ የአስተዳደር ስነስርዓት ህግ ማውጣቱ እንዲሁም የወንጀል ፍትህ አስተዳደሩን አስመልክቶ ከዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር የተጀመሩ ቅንጅታዊ አሰራሮች የማጠናከር ሥራዎች መከናወናቸው ተገልጿል፡፡

በማህበረሰቡን መሰረት ያደረጉ ባህላዊ አማራጭ የግጭት መፍቻዎ ሥርዓቶችን በህግ በማስደገፍ ወደ ስራ ከማስገባት፤ የአስተዳደር ህጉን በተሟላ መልኩ ተግባረዊ በማድረግ ረገድ እንዲሁም ማረሚያ ቤቶችን ከማሻሻል ጋር ተያይዞ የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናከር እና ሌሎች በዘርፉ የታቀዱ ስራዎችን በቀሪ ጊዚያት እንዲጠናቀቁ በተለይም ስራዎችን በቴክኖሎጂ አስደግፎ ከመስራት አኳያ ስር ነቀል እርምጃዎችን መወሰድ እንደሚገባ በምልከታ ሂደቱ ተጠቁሟል፡፡

የትራንስፎርሜሽኑ ቀሪ ስራዎች በክልሉ በጀት እና ከአጋር ድርጅቶች በመቀናጀት በተፋጠነ እቅድ በመመራት ስራዎቹን ለማጠናቀቅ ጥረት እንዲደረግ በክቡር አቶ ኡመድ ኡጁሉ አቅጣጫ ተሰጥቶ እና በጋምቤላ ከተማ የተቀናጀ የፍትሕ አካላት አንድ ማዕከልን አገልግሎት በመጎብኘት ክትትሉ ተጠናቋል፡፡

በተደረገው ውይይት የክልሉ ምክር ቤት አፈጉባኤ፤ የክልሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግና ፍትህ አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ፤ የፍትህ ቢሮ አመራሮች፤ የክልሉ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት፤ የማረሚያ ቤት ኮሚሽን ኮሚሽነር ተገኝተዋል፡፡

Tagged Under: african charter on the rights and welfare of the child • budget year performance • budget year plan • conduct • Convention on the Rights of the Child • convention on the rights of the child (crc) • ethiopia's justice sector • ethiopian justice sector • formation • gambella • Gambella Region • government law and justice services sector • Justice • Justice Sector • Justice Sector Transformation • Justice Sector Transformation Plan • justice transformation plan • monitoring • per • performance • plan • region • ring • sector • three-year justice sector transformation plan • transformation • transformation plan • year
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች