በአፋር ክልል በሰብዓዊ መብቶች አያያዝ፣ በአገራዊ የሰብዊ መብት ክትትል እና የዓለም ዓቀፍ የሕግ ድንጋጌዎች አተገባበር ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጠ

A training focused on human rights handling, national human rights monitoring, and the implementation of international legal provisions was given in the Afar Region.

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የሰብዓዊ መብቶች ዳይሬክቶሬት ከተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) ጋር በመተባበር በክልሉ ለሚገኙ የፍትሕ ተÌማት እና የሰብዓዊ መብቶች አመራሮች እና ባለሙያዎች በሰብዓዊ መብቶች አያያዝ፣ በአገራዊ የሰብዓዊ መብት ክትትል እና የዓለም ዓቀፍ የሕግ ድንጋጌዎች አተገባበር ላይ ያተኮረ ሥልጠና በሠመራ ከተማ ለሁለት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ ቆይቷል፡፡

የሥልጠናዉ ዋና ዓላማ በሰብዓዊ መብቶች በተለይም በጥበቃ ሥር ያሉ እና በፍርድ ቤት ትዕዛዝ የታሰሩ ሰዎች መብት አፈጻጸም መርሆዎች ላይ የሰልጣኞችን ክህሎት ማሳደግ መሆኑም ተመላክቷል፡፡

የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክር ቤት ም/አፈጉባኤ ክብርት ወ/ሮ መይረም መሀመድን ጨምሮ ከክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ ከፍትሕ ቢሮ፣ ከፖሊስ ኮሚሽን እና ማረሚያ ቤቶች የተወከሉ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች በሥልጠናው የተሳተፉ ሲሆን፣ መድረኩ ባለፉት ዓመታት የነበሩ ክፍተቶችን በመለየት በቀጣይ ለማሻሻል የሚያስችል ክህሎት ለማግኘት እንደሚያግዝ ምክትል አፈጉባኤዋ ገልጸዋል።

መድረኩ የፍትሕ ሚኒስቴር የሰብዓዊ መብቶች ክትትል ማኑዋል፣ የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ሪፖርት፣ ምክረ ሃሳቦች እና ሁሉን ዐቀፍ ወቅታዊ ግምገማ ላይ ያተኮሩ ሃሳቦች፣ የተጠርጣሪዎች እና ታራሚዎች መብቶችን የሚደነግጉ ዓለም አቀፍ የህግ ማዕቀፎች፣ እንዲሁም በክልሉ ከሚገኙ ማረሚያ ቤቶች አንዱ በሆነው የአሳይታ ማረሚያ ቤት ጉብኝት የተደረገ እና በጉብኝቱ የተስተዋሉ ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች እንዲሁም ዐበይት ምክረ ሀሳቦች እና የማስፈጸሚያ ስልቶች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

በተጨማሪም ኢትዮጵያ በተቀበለቻቸዉ ዓለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብት ድንጋጊዎች አተገባበር ላይ የታዩ ክፍተቶች እና ተግዳሮቶች በሥልጠናዉ ላይ የተወሱ ሲሆን በ2018 በጀት ዓመት እንደ ሀገር የተቀበልናቸዉን ምክረ ሀሳቦች ለመፈጸም ፍኖተ ካርታ እና የድርጊት መርሀ ግብር ማዉጣት፣የፌደራል እና የክልል ማረሚያ ቤቶችን መጎብኘት፣አገራዊ የአፈጻጸም ሪፖርትን አዘጋጅቶ ማቅረብ እና የአገሪቱን የጋራ ዋና ሰነድ( Common Core Document) አሻሽሎ ማቅረብ ዋነኛ የትኩረት አቅጣቻዎች እንደሆኑ ተጠቁሟል፡፡

Tagged Under: Afar • Afar Region • common • document • handling • human • Human Rights • human rights monitoring • Implementation • international • judicial • legal • Legal Provisions • monitoring • National • pro • provision • provisions • region • right • Rights • ring • Training • un • UNDP • Use • used • vision
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች