ለሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አስፈፃሚ መ/ቤቶች መካከለኛ አመራሮች በአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት ህግ ላይ ስልጠና መሰጠት ተጀመረ

Training on Administrative Procedure Law Begins for Middle-Level Leaders of Sidama National Regional State Executive Offices

በኢ.ፌ.ድ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር በንቃተ ሕግ ትምህርትና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት በሲዳማ ክልል ለሚገኙ አስፈፃሚ መ/ቤቶች መካከለኛ አመራሮች አስተዳደር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ላይ ከህዳር 03 እስከ 04 ቀን 2017 ዓ.ም ለሁለት ቀናት የሚቆይ ሥልጠና በሀዋሳ ከተማ እየተሰጠ ነው።

ሥልጠናው ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉልን በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፍትሕ ቢሮ ምክትል የቢሮ ሃላፊና የሕግ ጉዳዮች ዘርፍ ሀላፊ የሆኑት ወ/ሮ አሽሌ ዳንኤል የአስተዳደር ጉዳዮችን በተመለከተ መንግስታዊ አሠራር ለሕዝብ ግልፅ በሆነ መንገድ መከናወን እንዳለበትና አስተዳደራዊ ውሳኔ ለመስጠት በማስፈለጉ የፌድራል የአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት ህጉን ተከትሎ ክልሉ የክልሉን የሥነ ስርዓት ሕግ ማጽደቁን ገልፀዋል።

አክለውም ለምናገለግለው ሕዝብ በመንግሥትና በሕዝብ መካከል ያለውን አመኔታ ከፍ ለማድረግ እንዲሁም የሕዝብ አገልግሎትን ለማሳለጥ አዋጁ ላይ ግልጽነት ለመጨመርና ዕውቀትና ክህሎታችንን ለማዳበር ሥልጠናው አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ንቃተ ሕግ ትምህርትና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ስምረት ታደሰ እንደገለጹት የአስተዳደር ሥነ ስርዓት ህጉን ሌሎች ክልሎችም ማጽደቃቸውን ገልጸው የፍትሕ ሚኒስተር ለክልሎች ድጋፍ እያደረገ መሆኑን እና ድጋፉ ቀጣይነት እንደሚኖረው ገልፀዋል።

ሥልጠናው በዋናነት የአስተዳደር ስነ-ስርዓት ሕግ ምንነትእና ጠቀሜታ፣ የአስተዳደር መመሪያ አወጣጥ ስነ-ስርዓት፣ የአስተዳደራዊ ውሳኔ አሰጣጥ ሂደት፣ የፍርድ ቤት ክለሳ እንዲሁም በህጉ የዜጎች መብት እና የአስፈፃሚ አካላት ግዴታ ላይ ያተኮረ ነው፡፡

ሥልጠናው በፍትሕ ሚኒስቴር ንቃተ ሕግ ትምህርትና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት ምክትል ዳይሬክተር በሆኑት ወ/ሮ ስምረት ታደሰ እና በዳሬክቶሬቱ ዐቃቤ ሕግ የሆኑት አቶ መስፍን መኮንን የሚሰጥ መሆኑ ተጠቅሷል።

Tagged Under: Administrative Law • Capacity Building • Legal Training • Public Administration • Sidama Region
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች

ተመሳሳይ ዜናዎች